Thursday 23 August 2018

የሊቀ ጳጳሳት ፍራንሲስ ማሳሰቢያ ኹላችንን አይመለከትምን?

    የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ፣ “ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በቀሳውስቷ በልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወሲባዊ ጥቃት የመከላከል እንዲህ ያለ አድራጐት ተፈጽሞ ቢገኝ እንኳ አንዳትሸፋፍን የሚያደርግ ባህል ለማረጋገጥ አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ እንዳለበት” ዛሬ ከጽሕፈት ቤታቸው አስታውቀዋል። ይህ እጅግ አስደናቂም አሰቃቂም ውሳኔ ነው፤ ይህን ስሰማ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ባለ ነውር ተጠልፋ መውደቋን ደጋግሜ አሰብሁ፤ ውስጤም በጽዩፍ መንፈስ ኾኖ ተቈጣ።



   እውነት ነው፤ በአኹን ሰዓት በመካከላችን የሚሰሙ እጅግ አስነዋሪ ኃጢአቶች አሉ፤ አብያተ ክርስቲያናት “ከሠላምና ከወንጌል አዋጅ” ውጪ፣ የሰቆቃና የዋይታ ድምጾችም የሚሰሙባቸው ሥፍራዎች ከኾኑ ሰነባብተዋል። የዛሬ ሦስት ዓመት ገደማ በሻሸመኔዋ - ኩየራ፣ አንድ ጣሊያናዊ የደብር አለቃ ከሦስት ሕፃናት በላይ ላይ የግብረ ሰዶም ጥቃት አድርሶ፣ ከነቪዲዮውና ምስሎች ተይዞ፣ በጓደኛ መነኮሳቱ ትብብርና በፍትህ ሥርዓት አስከባሪዎች [በተለይ ፍርድ ቤት] ልልነት ምክንያት በዋስትና በመለቀቁ ምክንያት ወዲያው አገር ለቅቆ ወጣ።
  ሳይዘገይ፣ በዚው አከባቢ አንዲት ሴት በአንድ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ቄስ ተደፍራ፣ “የቤተ ክርስቲያንን ክብር ይነካል በሚል ፈሊጥ ተሸፋፍኖና ተድበስብሶ” ታለፈ። በቅርቡ ደግሞ አንዲት እህት የዩንቨርሲቲ ትምህርቷን ልትመረቅ በመጨረሻው ዓመት ላይ ሳለች፣ መምህሯ ቤተ ክርስቲያን ይቀጥራታል፤ “መንፈሳዊ ትምህርቶችንም” ያስተምራታልና አልጠረጠረችም፤ ግን “የአስተማሪው” ሴሰኝነት ሳይቆይ ተገለጠ፤ እናም በግልጥ አሳፍራው ብትወጣም እንዳትመረቅ ውጤቷን እንዳበላሸባት ነገረችኝ፤ እኒህና ሌሎችም እጅግ ለጆሮ የሚዘገንኑ ተግባራት በእምነት ተቋማት ውስጥ ይፈጸማሉ፤ ግና “በጥብቅ ምስጢርነት ተይዘው” ተቀብረው ይቀራሉ። ተጐጂዎችም ከነጠባሳቸው ብቻቸውን በመቆዘም ይኖራሉ፤ ነገር ግን ስንቶችን መንፈስ ቅዱስ ረድቷቸው ከዚህ ክፉ ባርነት ወጥተው ይኾን?
  ብፁዕ አቡነ ፍራንሲስ የነገሩን የዝሙትና የሕፃናት ወሲብ ጥቃት ስፋትና የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተውታል ብዬ አስባለሁ፤ በተለይም ድርጊቱ የሚፈጸመው በሽሽግና ሰዋራ ቦታን በመምረጥ፣ እንዲሁም በተለይ ሴትና ሕፃናት ሲሆኑ፣ በወደ ፊት ሕይወታቸው ምንነትና በክብራቸውም ላይ የሚፈጸም ስለሆነ እጅግ ከባድ፣ ውስብስብና ለማስረጃ ፈታኝ የኾነ ድርጊት ነው። አድብተው የሚያጠቁት ሰዎች የወንጀሉን ባሕርይ በትክክል የተረዱት ይመስላል፤ እናም በተደጋጋሚነት ከመፈጸም የሚያግዳቸው የሌለ እስኪመስል ያደርጉታል።
  መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ባለ ርኩሰት ስለተያዙ ሰዎች በግልጥ ይናገረናል፤ “ዔሊም እጅግ አረጀ ልጆቹም በእስራኤል ሁሉ ላይ ያደረጉትን ሁሉ፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጅ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ።” (1ሳሙ. 2፥22) በማለት። ድርጊቱ እጅግ አስደንጋጭና ጆሮን ጭው የሚያደርግ ነው። ኃጢአት ምን ያህል የእግዚአብሔርን ጽድቅ ተጻራሪና ተቃዋሚ መኾኑን ፍጹም ማሳያ ነው። የዔሊ ልጆች እንዲህ ያለውን ነገር የወሰዱት ከአሕዛብ የአማልክት መንደሮች ነው።
   ይህ እጅግ አጸያፊ ነውር ያለው በከነዓናውያን ቤተ ጣዖቶች ውስጥ ነው፤ የእስራኤል ልጆች ግን ይህን የክፋትና የነውር ልምምድ ወደ ምድራቸውና ወደ አምልኮ ሥፍራዎቻቸው ጭምር አስገብተው ነበር፤ “በምድርም ውስጥ ሰዶማውያን ነበሩ ከእስራኤልም ልጆች ፊት እግዚአብሔር ያሳደዳቸውን የአሕዛብን ርኵሰት ሁሉ ያደርጉ ነበር።” እንዲል፤ (1ነገ. 14፥24)፤ በኢየሩሳሌም ነግሦ የነበረው ንጉሥ አሳ ከምድሪቱ ሰዶማውያንን [ግብረ ሰዶማውያንን] አስወገደ፤ አጠፋቸው (1ነገ. 15፥12)፤ አሳ ፈጽሞ ያላጠፋቸውንና የተረፉትን ግብረ ሰዶማውያንን ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ከምድሪቱ ጨርሶ አጠፋቸው፤ (1ነገ. 22፥46)።
   በሕጉ በግልጥ ቃል፣ “ከእስራኤል ሴቶች ልጆች ሴት ጋለሞታ አትገኝ፥ ከእስራኤልም ወንዶች ልጆች ወንድ ጋለሞታ አይገኝ። ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የጋለሞታይቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አታቅርብ ሁለቱም በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና” (ዘዳግ. 23፥17-18) ተብሎ ተነግሯል፤ ነገር ግን የእስራኤል ቤት ብዙ ጊዜ ለዚህ ቅዱስ ሕግ መታዘዝን እንቢ አሉ፤ በዚህም እግዚአብሔርን ፈጽመው ተዳፈሩ፤ ቤቱንም አረከሱ፤ ኪዳኑንም አክፋፉ። “ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች ስለዚህ ረክሳለች ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ኀፍረተ ሥጋዋን አይተዋታልና አቃለሉአት፤ እርስዋም እየጮኸች ታለቅሳለች ወደ ኋላም ዘወር አለች። … አስጨናቂው በከበረ ነገርዋ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው አሕዛብ ወደ መቅደስዋ ሲገቡ አይታለችና።” (ሰቆ. 1፥8፤ 10) እንዲል፣ በኃጢአቷ ስለጸናች ሃፍረተ ሥጋዋ ታየ፤ ማንም ደግሞ ወደ እርሷ የሚገባባት ኾነች። አክባሪዋን ንቃለችና የሚንቋት ኹሉ ደፈሯት፤ የተከበረ ቅጥሯንም እንዳሻቸው ረገጡት።
  በአዲስ ኪዳንም እንዲህ ያለ ክስተት ተከስቶ ነበር፤ “በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።” (1ቆሮ. 5፥1) በማለት፣ በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን የዝሙት ዕድፈት ይነግረናል። ኃጢአትን በተመለከተ በብሉይም ኾነ በአዲስ ኪዳን የተለወጠ ነገር የለም። እግዚአብሔር ኃጢአትን አምርሮ ይጠየፋል፤ በልጁ ደም ለመታጠብ ፈቅደን ካልቀረብን በኃጢአት ምክንያት የሚመጣው የእግዚአብሔር ቁጣ ከእኛ ፈጽሞ አይርቅም፤ (ዮሐ. 3፥36)፤ የዕድሜ ርዝመት፣ የኃጢአት ትንሽና ትልቅ ፈጽሞ የሚረሳ አይደለም፤ ንስሐ ገብተን በልጁ አምነን በደሙ ታጥበን እስካልተመለስን ድረስ ቁጣው መቼም አለ።
  ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያለ ነውር በመካከሏ ሲገኝ፣ እንዲህ ያለው ኃጢአተኛ ሰው “መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ መፍረድ ይገባታል፣ (1ቆሮ. 5፥5) እንጂ፣ መሸፋፈንና መደባበቅ ፈጽሞ ከእርሷ አይጠበቅም። ይህን የምታደርግ ከኾነ፣ “የእግዚአብሔርን ልጅ ትረግጣለች፤ ያንንም የተቀደሰችበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር ትቆጥራለች፤ የጸጋውንም መንፈስ ታክፋፋለች፥ ታድያ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባት ይመስላችኋል?” (ዕብ. 10፥29)።
  ይህ ነገር ዛሬ እጅግ በብዙ አብያተ ክርስቲያናት እንደሚገኝ እውን ነው፤ ግና በመሸፋፈንና በማድበስበስ መታለፉ ነገሩን ይበልጥ ያጋግም እንደኾን እንጂ አንዳች መፍትሔ አያመጣም። በመካከላችን በዝሙት የሚከሰሱ አገልጋዮች እንዳሉ አንስትም፤ ነገር ግን ስንቶች እንዲህ ባለ ነገር አለመተባበራችንን በግልጥ፣ በዚህ ነውር የተያዙ ሰዎች እንዲመለሱ በማድረግ ደግሞ የምንተጋ እንኾንን? ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ራስዋን መመርመር እንዳለባት እናምናለን። ከለዘብተኝነትም ራሷን በቃሉ፣ በደሙና በቅዱስ መንፈስ በማንጻት ጨክና ልትቆም ይገባታል
  ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ በጣም ለዘብተኛ መኾኗን የሚያሳይ ሌላ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፤ ከጥቂት ወራት በፊት በአገራችን ኤች አይ ቪ ኤድስ ሥርጭቱ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ደርሶ እንደ ነበር በየመገናኛ ብዙሃን ሰምተን፣ ምንም ሳይቆይ “ኹሉም ነገር ፖለቲካ ኾነና” ዋናው ትውልድ የሚያነቅዘውና ምድሪቱን የሚያረክሰው ኤች አይ ቪ ኤድስ ተረሣ። እንግዲህ ምን ያህል ምድሪቱ ከእግዚአብሔር በእጅጉ እየራቀች መኾኗን የሚያሳይ ብዙ ማሳያ ማንሳት ይቻላል። [ከዚሁ ጋር በተያያዘ ደግሞ ኤርትራ ከአንድ በላይ ጋብቻ መፍቀዷን ስንቶች አስተውለን ይኾን? የኤርትራ አባቶችስ በዚህ ረገድ ድምጻቸው አለመሰማቱ ጉዟችን ወዴት ነው ሳያስብል ይቀራልን? (ገና ሕጉን ለማጽደቅ ስትዘጋጅ በዚህ ብሎግ የወጣውን ጽሑፍ መመልከት ይቻላል]
  በእግዚአብሔር ቤት ያሉቱ ስለኃጢአት አታድበስብሱ፣ አትሸፋፍኑ፣ አታመቻምቹ፣ አታለባብሱ ብሎ መለመን ምን ያህል ከመንገዱ መሳታችንንና የገዛ ነውራችን በእኛው ላይ እየመሰከረብን እንደ ኾነ ማስተዋል ይኖርብናል። እናም ራሳችንን በትክክል በእግዚአብሔር ፊት ማዋረድ ይኖብናል፤ ከጐናችን ወይም ከጐረቤታችን ወይም ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ነውር ያልተጠቃ ይኖር ይኾንን?! ስለዚህ ኹላችንን ይመለከተናል፤ ኃጢአትን አምርረን መጠየፍ ካልቻልን “እየኖርን ነው ያልነውን ክርስትና” መፈተሸና መመርመር አለብን። ሊቀ ጳጳሳቱ ከለመኑበት ልመና በሚበልጥ ስሜትና በመንፈሳዊ ግለት በትክክል ኃጢአትን መመረርና መጠየፍ አለብን፤ በተለይም በእግዚአብሔር ስም በተሰበሰበ ጉባኤ መካከል እንዲህ ያለ ነውር ስንሰማ ሊያመን፣ ሊሰቀጥጠን፣ ሊያሳቅቀን፣ ሊያሳፍረን፣ ሊያስለቅሰን፣ ሊያስቆጣን፣ ሊያንገበግበን፣ ውስጣችንን ሊያቃጥለን ይገባዋል፤ ይህ ካልኾነ እጅግ የሚያስፈራ ነገር እንደሚያገኘን ምንም መጠራጠር አይገባንም። የቤተ ክርስቲያን ማጫ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን ኃጢአትን የምትጠላበትን ጨካኝ መንፈስ ያድላት፤ አሜን

“አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።” (መዝ. 79፥9)።

17 comments:

  1. ፍራንሲስ ራሱ አይደለም እንዴ ወንጀሉ የሚያቀናብረው ወረኞች ሁላ

    ReplyDelete
  2. የ666 አራማጅ ከመቼ ጅምሮ ነው ሰባአዊ ነት የተሰማቸው?

    ReplyDelete
  3. የ666 አራማጅ ከ

    ReplyDelete
  4. ስለዚህ ሰው ምንም ኢንፎርሜሽን የለህም ።ግብረሰዶሞች በቤተክርስቲያን ውስጥ ጋብቻ እንዲፈጽሙ የፈቀደ ሰይጣን ነው

    ReplyDelete
  5. Tuuuu yihe wusha sewye!!! Sint hitsanat defroal sentunes ardoal...ye Lucifer chefra tuu

    ReplyDelete
  6. ይህ ሰውና አውሬ እኮ ነው የቫቲካን የካቶሊክ ጳጳስ አይደል? ዋና የኢሉሙናት ተወናዋኝ ነው እንንቃ

    ReplyDelete
  7. Gebere Sedomaweyanen Mereka Betselot yemetagaba Katolikawite sele gudau lemawerat men moral Yenoratal?

    ReplyDelete
  8. ይህ ሰው ዋሾ ነው በዛ ላይ ኢሉሚናንት ነው

    ReplyDelete
  9. 666 abal nw.... don't believe this men..........

    ReplyDelete
  10. Gebere Sedomaweyanen Mereka Betselot yemetagaba Katolikawite sele gudau lemawerat men moral Yenoratal?

    ReplyDelete
  11. እስካሁን ያነበብኩት ፊደል ያልቆጠሩ መሀይሞች የሚሰጡትን አስተያየት ነው፡፡ካቶሊክ እኮ ካቶሊክ ነው!!!

    ReplyDelete
  12. Lek belhal wedaje sewyew ersu cheger yalbet aydel yemn meterarat nw

    ReplyDelete
  13. The pontiff himself is a serious contiguous disease. I am expecting the Lord God to give him wage for he did and is doing. What a disgrace for Christianity.

    ReplyDelete
  14. The pontiff himself is a serious contiguous disease. I am expecting the Lord God to give him wage for he did and is doing. What a disgrace for Christianity.

    ReplyDelete
  15. ...Nice pop frances

    ReplyDelete
  16. Firasisko Malet ye seyitan mahiberechi wana halafi New selesu mininet (ye satinaali Goli Ethiopia lay tagegnutalachu part 1&2Hulet etim

    ReplyDelete
  17. Des yemel neger benor egna catolicawyanoch mhirt enlemenalen enje anragemem abatachen feranses eg.r yetbkiln amaaan i miss catolic

    ReplyDelete