Sunday 10 September 2017

ሠርክ አዲስ ዘመኔ!

Please read in PDF


ለምንድር ነው እንባ ስለምንስ ልቅሶ?
ከዘመናት በፊት ደምህ ለ‘ኔ ፈሶ፤
ሰቀቀን ለምኔ ማፈርና ፍርሃት?

ለኀጢአተኛ ልጅህ ውዴ ሞተህለት፤
ክረምት ጨለማ በ‘ኔ አይሰለጥንም፤
ማርጀትና መርገም ደጆቼን አይረግጡም፡፡
ከዚህ የተነሣ …
ሰው እንደሚቆጥረው ዘመንን አልቆጥርም፤
ባ‘ንተ አዲስ ሆኜ አሮጌ አልናፍቅም፤
ንጋቴ ነህ ጌታ ለእያንዳንዱ ቀኔ፤
ዘወትር እንቁጣጣሽ ሠርክ አዲስ ዘመኔ!

1 comment:

  1. ሰው እንደሚቆጥረው ዘመንን አልቆጥርም፤
    ባ‘ንተ አዲስ ሆኜ አሮጌ አልናፍቅም፤
    ንጋቴ ነህ ጌታ ለእያንዳንዱ ቀኔ፤
    ዘወትር እንቁጣጣሽ ሠርክ አዲስ ዘመኔ!amen

    ReplyDelete