Monday 25 September 2017

መስቀል ማለት ለኔ …

          Please read in PDF

መስቀል ማለት ለኔ …
ጌታዬ ኢየሱስ እኔን ስለመውደድ
ሊያድነኝ ሊቤዠኝ የሄደበት መንገድ
ከጲላጦስ ሄሮድስ ከሄሮድስ ጲላጦስ

የተንገላታበት በከለሜዳ ልብስ …
መስቀል ማለት ለኔ ሕማምና ሞቱ
መገፋት መውደቁ ችንካርና ደሙ!
እሱን ነው የምለው መመኪያ ቤዛዬ
ታትሜ ምዞረው በነፍስ በሥጋዬ!
እናም …!
ስሰብክ ስዘምረው መቼም ማላፍርበት

ይኼ ነው መስቀሉ ይህ ነው  የ’ኔ ሕይወት!

No comments:

Post a Comment