Friday 17 February 2017

በችኩል አገልጋይ

Please read in PDf


ስርጓጉጥ ሳይጠራ
መንገዱ ሳይቀና
ኮረብታው ዝቅ ብሎ
ሸለቆው ደልድሎ
ለመረማመጃ ሳይደላ በቅጡ
እሩጫው ወዴት ነው፣ ችኮላው ምንድር ነው፣ ሳያጠባብቁ?


ዘርን የሚዘራ ልከኛ ገበሬ
ተላላ አይደለም፣ ተዘልሎ አይደለም፣ ‘ሚጠብቀው ፍሬ
ለፍቶ ባጅቶ ጥሮ
ወዝ ጥሪት አፍስሶ
ደጋግሞ ደጋግሞ መሬት አለስልሶ
በብዙ ድካም ነው ለፍሬ ሚጓጓው
እንጂ ባንድ ጀንበር፣ ‘ራሱን በመንጨት፣ አይልም ለምን ነው?

መንገድ ሳያበጁ
እርሻውን የሰው ልብ ሳያዘገጃጁ
ድንገት ዘርን ዘርተው ፍሬ ‘ሚጠብቁ
መንገድና ጭንጫን እሾኹን ረስተዋል

ዘሩ እንከን ሳኖረው፣ በችኩል ሩጫቸው ፍሬ አልባ ሆነዋል፡፡

3 comments:

  1. ጌታ በነገር ሁሉ ማስተዋልን ስላበዛልህ እናመሰግነዋለን

    ReplyDelete
  2. Amazing Discovery !!!

    ReplyDelete