Tuesday 21 February 2017

መምጣቱን እናድንቅ


Please read in PDF


የባሪያውን ልብስ

አድርጎ እንደክት

ገረዲቱን ሊያከብር


ዘርግቶ የክብር ወንበር

በፉጨት ድምጽ ሊሰበስብ ጠርቶ

እርሱን እንድንመስል እያስዋበ ቀርጾ፤

ከዘላለም የጽድቅ መንግሥቱ

በአንድ መንጋ በበረቱ

ሊኖር ተከቦ በወዳጆቹ

ወረደ የክብራችን ሰገነቱ፡፡

የትንቢት ቃል ሊዘጋ

ሆኖልን ፍጻሜ ኦሜጋ፡፡

በጠላት ፊት ሊፈላ ዘይቱ

ሊያሰፋን በርስቱ

ወረደ አክባሪው

እኛን ሠሪው፡፡

ወንጌልን ለድሆች

ብሎ የምስራች

እስራትን ፈቶ

ሞትን ውጦ ረ‘ቶ

ማየትና መስማት

ድንቅ ተአምራት

ጽድቅ እያረበበ

ፍቅር እየመገበ

ሊያኖረን ነው ጌታ ከሰማይ መውረዱ

እንዲያው ያለዋጋ እኛንም መውደዱ፡፡

እንኪያ ተወዳጆች!

የእርሱ ባለሟሎች

ድካማችን ሊያግዝ

ደግፎንም ሊይዝ

እርሱ ለከፍታ ከሆነ የመጣው

የእኛ ወደ ውርደት መንደርደር ምንድር ነው?

በሚተጋ ጽናት በታገሰ ጸሎት

በተወደደ ቃል በጾምና ምፅዋት

መምጣቱን እናድንቅ ከሰማይ መንበሩ

በእርሱ እንድንከተት ከጽድቅ ሀገሩ፡፡


1 comment:

  1. ጌታ ጸጋ ስላፈሰሰልህ ስሙ ቡሩክ ይሁን

    ReplyDelete