Tuesday 28 February 2017

ቅድስት ሰንበቴ

አልቅበዘበዝም እረኛ እንደሌለው
ከቶ አልጨነቅም ጥጉን እንዳጣ ሰው …

ከሰሎሞን ይልቅ ከሙሴም ሰንበታት
በኢያሱ አንደበት ከታወጀው እረፍት
ከሁሉም የምትበልጥ የዘውትር ሐሴቴ
‘ሚመስልህ የሌለ አንተ ነህ እረፍቴ
ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ሰንበቴ!


3 comments: