Thursday, 14 May 2015

ከሳሽ ዕድፉን ሳያይ ...


               Please read in PDF
         

ስታመነዝር አገኘናት፣
ብለው አካልበዋት፣
ከጌታ ፊት እያቻኮሉ፣
ከእግሩ ሥር አምጥተዋት ጣሉ፡፡

ምን ትላለህ? ስለዚህም ሴት፣
ይዘናታል በማመንዘር ኃጢአት፣
ሙሴ እንደው በሕጉ፣
ብሎናል ወግራችሁ ግደሉ፣
አንተስ ምን ትላለህ?
ይሰማ እስኪ ፍርድህ … ?

ይላሉ ከሳሾች …
ወንዱን አስመልጠው ፣ ሴቷን አሳዳጆች፤
እውነት አንሻፋፊ ፣ ግማሽ ምስክሮች፤

ኢየሱስ መለሰ …
ጐንበስ ብሎ ከምድር ፣ አንዳች እየጻፈ፤
ከʻናንተ መካከል ፣ ነውሯ ያላገኘው፤
ድንጋይን ከሯሷ ፣ አሁኑ ይጫነው፤
ብሎ ሳያበቃ ፣ ቀና ሲል ካለበት፤
ከʻርሷ በቀር የለም ፣ ከተከሳሿ ሴት ፤
ለካስ ሁሉም ጥሎ ፣ ከዚያ ሥፍራ የጠፋው፤
ከʻርሷ ጋር ተጋድሞ ፣ ዕድፉን ባያየው ነው፡፡

ያመነች ግን እርሷ ፣ ተከናወነላት ፤

መንገዷን ቀየረች ፣ ከሞት ወደሕይወት፡፡

No comments:

Post a Comment