Thursday 26 June 2014

ሰቀሉህ ብዬማ እኔስ አላነባ!

Please read in PDF:- sekeluh byema enes alaneba!

ስለአይሁድ ጅራፍ፤ ችንካርና እንግልት፣
ስለ አክሊለ እሾሁ ሚስማርና ቁስለት፣
ጎንህ በጦር  ስለት ስለመወጋቱ፣
በጠቆረ ህሊና በዘንግ መቀጥቀጡ፣
ለሞት ለመቃብር ይህ አላበቃህም፣
ባለብዙ ምህረት ኢየሱስ መድህን፡፡

     የግፍ ግፋታቸው በጥላቻ ገፍቶህ፣
     የአመጻ ፍትህ አሽቀንጥሮ ደፍቶህ፣
     በማይራራ መዳፍ ከግንድ እያማቱ ፣
     በደል ሳያገኙ ባ’ድማ እየተንጫጩ፣
     አቁመው ዕርቃንህን የኋሊት ጠፍረው፣
     ስላሉህ አይደለም ስቀለው! ስቀለው!
     የ’ኔን ሞት ጌታዬ አንተ ለ’ኔ የሞትከው፡፡



አንተማ የሞትከው እኔን ስለማፍቀር፣
እኔን ስለመውደድ እኔን ስለማክበር፣
ስለእኔ ነው ጌታ ስለባዘንኩ በግህ፣
መገረፍ መቁሰልህ መቃብር መውረድህ፣
ለ’ኔማ ነው የሞትከው የረከስኩ እንድጸድቅ፣
እንዲሁ በጸጋ ወደእልፍኝህ ልዘልቅ፣
እንዲህ ነው የማምንህ አንተን የ’ኔን ቤዛ፣
ለ’ኔ እየወደቅህ እኔ እንድነሳ፡፡
    እንኪያ … !
    ገደሉህ፤ ሰቀሉህ ብዬማ አላነባ?፣
    ሞትክልኝ ብዬ እንጂ የሳቅ ዜማ ላምጣ፡፡
           አዎን የ’ኔ ጌታ ታርደሃልና ፤ታርደሃልና ፣
           ትንበርከክ ነፍሴ ለሞቷ ሞተህ ቆማለችና፡፡


No comments:

Post a Comment