Monday 2 June 2014

እንዲሁ ይመጣል!

Please read in PDF :- Indihu yimetal!
ለምን ነው ‘ምታዩት እንዲህ አንጋጣቹ’፤
ወደሰማይ ፋና አይና‘ቹን ልካቹ’፤
በነፍስ ትካዜ በመንፈስ ታክታ’ቹ … ? ፤
ሳይረቅ እየራቀ ሲሄድ የምታዩት፤

የአለሙ ሁሉ ቤዛና መድኃኒት፤
እንዲሁ ይመጣል ድንገት እንደሌባ፤
ተጽናኑ ታገሱ ሆዳችሁ አይባባ፡፡

ጸሎት ሳይታጎል ወንጌሉ ሳይጎድል፤
ተግታችሁ በመቅደስ ጠብቁት በፍቅር፤
ይመጣል በክብሩ ያ ያረገው ጌታ፤
በግርማ መለኮት በክበበ “ሥጋ”፡፡

የዘገየ መስሎ አገልጋይ ‘ምትገፉ፤
የ“አይመጣም” ስብከት የምትለፈልፉ፤
ዘመን ከመዋጀት በአመጽ ‘ምትሰንፉ፤
ይመጣል ዳግመኛ የናዝሬቱ ኢየሱስ፤
ታማኝ ባርያዎቹን ጸጋውን በማውረስ፤

ኃጢአትን ሊቀጣ ዘለዓለም ሊነግስ፡፡

4 comments:

  1. አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና!!!

    ReplyDelete
  2. betame merete wenegalawi geteme

    ReplyDelete
  3. amen amen amen.

    ReplyDelete
  4. ewnete new yetegefu miyarefubet gizea kenegusu gare minegesubete seate yemetale tebareke wenedemea gerum difek

    ReplyDelete