Wednesday 11 June 2014

የኢየሱስ ዝቅታ …

Please read in PDF :- yeEyesus zikta

ሐማዊ ከፍታ …
ሰማይ ሰማይ ሰማይ - አርጤክስስ ዙፋን ሥር፤
ከዚያ ዝቅ ሲሉ - ሌላ ሥፍራ የለም - ከመቃብር በቀር፡፡
     የኢየሱስ ዝቅታ …

     ዝቅ ዝቅ ማለት - አለልክ ዝቅታ፣
     ዋጋው በሰማያት - ከፍ ከፍ ማለት - አለልክ ከፍታ፤
     ባ‘ብ ፊት ከበሬታ … ፡፡
ሐማን እያወረድን - ኢየሱስን ‘ምንሰቅል፤
እኛ የዚህ ዘመን - የይሁዲ ዘር ነን፤
ከትዕቢት መድረክ - ወደትህትና፤
ልባችን በፍቅር - ወዶ ካላቀና ፤
ከ‘ኛ በታች በታች - ሌላ ማን አለና!? 
     መጠቃት ቢመስልም - የኢየሱስ ዝቅታ፤
     ልባችን አይሻ - የሐማን ከፍታ፤
     ዝቅ ዝቅ ብለን - ትህትናን እንልመድ፤

     ይህ ነው የክብርና - የኢየሱስ መንገድ፡፡

1 comment: