Wednesday 30 October 2013

ይሟገትልኛል



መታጠቂያውን ታጥቆ
በስጦታ ብዛት አፉን ስሎ
ሊራገም ሊያራኩት
እዚያው ቀልጦ ሊያስቀር በምድረ በዳው ውስጥ
በምዋርት በአስማቱ
ጉዟቸውን ሊያደርግ ራዕይ አልባ ገልቱ
በለአም በባላቅ ተመክሮ ተዘክሮ
ማለዳ ተነስቷል ሊያስቀር አቅልጦ
እንደቅጠል ሊያረግፍ በእንጭጩ አምክኖ፡፡


          እስራኤል አያውቅም ይህን እልፍ ተግዳሮት
          ሲረገም ሲጠላ በአስማትና ምዋርት
          በድንኳኑ ሆኖ ተዘልሎ አርፏል
          ስለእርሱ አዶናይ ተግቶ ይሟገታል
          ነገር ተቀይሯል
          ረጋሚው መባረክ ማመስገን ጀምሯል፡፡
ረጋሚው ቢረግምም
ሥር ማሹ ቢቀምም
አሟራቹ ሟርቶ በአስማቱ ቢመካም
የመለኮት ጥላ በዙርያዬ ረቦ
ይሟገትልኛል ጠላቴን አጽንቶ
አብዝቼ ሳልሰለች እባርክሃልለሁ
ከማላውቀው ጠላት ጌታ አድነኸኝ አሁን አይቻለሁ፡፡

5 comments:

  1. Yegna geta yetemesegene yhun

    ReplyDelete
  2. Yegna geta yetemesegene yihun amen

    ReplyDelete
  3. አሜን የኛ ጌታ የተመሰገነ ይሁን።

    ReplyDelete
  4. AMEN SEMU YIKBER

    ReplyDelete