Thursday 17 October 2013

እጅጉን ቀላል ናት

ከባድማ አይደለም የማይቻል ነገር
በፍቅር የታዘዝነው የጌታችን ወንጌል
በጣት 'ማይነካ አስቸጋሪና ጭንቅ
አይደለችም ወንጌል የአምላካችን መንገድ፡፡

         ከባዱ ሌላ ነው እጅግ አስጨናቂው


         በደም የተዋጀ ይህን የጌታ አካል
         በዝሙት በዘፈን በስካር ማቃጠል
         ወስዶ ከአጋንንት በአንድ ማዳበል
         ይህ ነው 'ማይቻለው ለጌታ ተመርጦ
         ማገልገል ሰይጣንን ገሃነምን ወዶ

እንጂማ የጌታ ክርስቶስ ፈቃዱ

እጅጉን ቀላል ናት አጥበው ልብሳቸውን በደሙ ላነጹ፡፡

1 comment: