Tuesday 1 October 2013

ተፈስሒ ፍስህት



የኢየሱስ እናቱ እጅግ ደስ ይበልሽ
ተወዳጅ አማኑኤል ፀጋ ስለሰጠሽ
 ደስ ይበልሽ ደስታን ጮኸሽ ተናገሪ
ስለመድኃኒትሽ በእልልታ  ዘምሪ

      አንቺ የእምነት እናት ደገኛ ሙሽራ
      የተሠራሽ በእጁ ለቅዱሱ ሥራ
      በእምነት ትከሻ አካላዊ ቃልን
      በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የማይቻለውን
      ይዘሽ የታየሽው ገሊላዊት ድንግል
      ደስ ይበልሽ ፍጹም ደስታ  ይገባሻል


ከነሳምሶን ሁሉ በልዩ ናዝራዊ
ቃሉን በእምነት ልብ ያመንሽ ወንጌላዊ
የትህትና አብነት ኪዳኑን 'ማትረሺ
የደመቀ ስሙን ስታሞጋግሺ
ተመሰጠ ልቤ  አወደው ፀሎትሽ
የረዳሽን አምላክ አመሰንኩ ልጅሽ

     ደስ ይበልሽ ድንግል ተፈስሒ ፍስህት
     ድንቅ አድርጓል ባንቺ የዘላለም አባት
     ደስታሽ የመነጨው ከሥላሴ ዙፋን
     ሞልቶ ይፈሳል እንጂ ማን ሊያቆም ይችላል?
     በልጅሽ የምናምን እኛም ወዳጆችሽ
     እንዳንቺ ከፀናን መንግስቱን ነን ወራሽ፡፡


No comments:

Post a Comment