Sunday 6 October 2013

ቆርጠህ ለየን ጌታ



ትዳሩ ጠነዛ
ቀለበት አርፍዶ - ስለተነጠፈ አልጋው በማለዳ
መድረኩ አረጀ   
ክርስቶስ ተረስቶ - የሰባኪው ስኬት ጊዜ እየፈጀ
ምጽዋቱ ሻገተ



ቀኝ እጅ መወደስን ከግራ እየሻተ
መልካምነታችን ገረጀፈ በዝቶ
ባንተ መቀደስን "ጽድቃችን 'ረስቶ"
ከራስ መልካምነት ከፊታችን በጎ
ቆርጠህ ለየን ጌታ ከሽንገላ አምልኮ፡፡
     

No comments:

Post a Comment