Saturday 21 September 2013

ያኖራል መዓዛው



የሳሮን አበባ - ፅጌረዳም አይደል
የህብረ ቀለማት - የውበትም ፀዳል
የሚማርክ ነገር - ፍፁም የለበትም
መዓዛው ሌላ ነው - አይደል  የሰሊክም
'ሚሸተው ሌላ ነው - ሮማንም አይመስልም፡፡
ሽቱ አርከፍክፎ
ሱፍ ከረባት ለብሶ
ቁመቱ ቢያማልል
መልኩ ቢያነሆልል
ቃሉ ምን ቢማርክ


አንጡር ሀብት ቢኖረው
አዝማዱ ቢከበው
ይመስልሐል እንጂ …
ከኃጢአት ቤት ከቶ ምንም መልካም የለው
መዓዛው ጠረኑ ለነፍስ ርኩሰት ነው፡፡

አማናዊ ሳሮን አማናዊ ሮማን
ለቆሸሸ ኃጥዕ ለረከሰ አማኝ
ክርስቶስ ብቻ ነው ንፁህ ንዑድ ሽቶ
ከዕጣን ከሰሊክ ከሁሉም በልጦ
ያኖራል መዓዛው በፍፁም ተመስጦ፡፡ 

4 comments: