በዕድሜ ስልቻ በዘመን ቀልቀሎ
ሰው እንዴት ይኖራል ምንም ተሸክሞ?...
ጽድቁ የመርገም ጨርቅ
በጎነቱ ፍትፍትና ምርቅ
መልካምነቱ አሮጌ እራፊ
አሳዳጅና ክፉ ቀሳፊ
ነግሶ ሳለ በዚያ ዘመን
ይገርመኛል ይደንቀኛል እኔን!!!
እድሜ ተንበሻብሾ
መስፈሪያውን ጥሶ
እንዴት ኖረ? እያልኩኝ
እገረማለሁኝ!!!
ሴት ማቱሳላ ያሬድ መላልኤል
ላሜህ ሄኖክ አዳም ኖህና ቃይናን
እንዴት ነው የኖሩት
ምንስ ነው የሰሩት?!....
ሙሴና ሳሙኤል በመስፈሪያ እድሜቸው
ሥራቸውን ትውልድ ከወደደላቸው
ምንድር ነው ግትልትል የእድሜ ዘባተሎ?
ምኑንም ሳይዙ ሁሉን አንጠልጥሎ
እንግዲህ ፍጻሜው እንደዚህ ይጠቅለል
ዘጠኝ መቶ አመት የሞተ ሰው ኖሯል!!!
ያልሰሩበት ዕድሜ ምን እንደው ቢበዛ
ሺሁ 'ለት አይሞላም እንደማቱሳላ!!!
አቦ! ጸጋና ማስተዋሉን ያብዛልህ፡፡ቡሩክ ሁን እጅህን ያለምልመው፡፡ቃለ ህይወት ያሰማህ፡፡
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማህ፡፡
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማህ፡፡
ReplyDelete