Friday 2 August 2013

የተሰሎንቄ እብዶች


     በቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞዎች ከማይረሱ ከተሞች መካከል አንዷ ተሰሎንቄ ናት፡፡ ከአውሮፓ ወደእስያ ለሚዘዋወረው ሰውና ንግድ ዋና የባህር በር ሆና የሰረገላም መንገድ ተሰርቶባት ያለችግር መመላለሻ ነበረች፡፡ከተማይቱ ብዙ የአይሁድ እምነት ተከታዮች ያሉባትና እኒህም ምኩራብ ሰርተው ያመልኩ የነበሩ ናቸው፡፡
        የሐዋርያት ሥራን የዘገበልን ቅዱሱ ተጓዥ ሉቃስ ቅዱስ ጳውሎስ ወደዚህች ከተማ መጥቶ ሦስት ሰንበት ያህል ከመጽሐፍ እየጠቀሰ " … ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ፦ ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው" እያለ ተርጉሞ በማስተማሩ "ከእነርሱም አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ" ይለናል (ሐዋ.17÷1-4)፡፡

       የክርስትና የስብከት ማዕከላዊ ርዕስ ኢየሱስ የሆነ ክርስቶስ እርሱ መሲህ ነው የሚለው ነው፡፡ዛሬም ድረስ ይህ እውነተኛ የሐዋርያት ትምህርት "ታላላቅ" እንደሆኑ ለሚያስቡ አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀር የመለያየት ምልክት ነው፡፡ ኢየሱስ በሚለው ስም ከአይሁድ እስከአህዛብ አይደለም ብለው አይሟገቱም፡፡ ክርስቶስ እርሱ ብቃት ያለው አዳኝ ነው የሚለው ሲጨመር ግን አብዛኛው ጉርምርምታና ጆሮውን ማከክ ይጀምራል፡፡ የሐዋርያት ሥራን ስናጠና የሐዋርያት የመከራቸውና የመሰደዳቸው መነሻና ድምዳሜው እንዲህ ብለው ጮኸው መስበካቸው ነው፡፡
          እንግዲህ ይህን ማስተማር ከውግዘት እስከመግደል ሊያደርስ ይችላል፡፡ በተሰሎንቄ የሆነው ይህ ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ከጥቂት የዘለሉ ያመኑትን ያዩ የበዙት የተሰሎንቄ "አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ…"(ቁ.5)፡፡ አስተውሉ!!! ወንጌሉን የሰሙ አምነዋል፡፡ ያልሰሙና መስማት የማይፈልጉ ግን ሁሌም ይበጠብጣሉ፡፡ዛሬም ለቤተ ክርስቲያን ራስ ምታት የሚሆኑት ቃሉን ለሁል ጊዜ የሚሰሙትና ኃጢአትን የጠሉ እውነተኛ ክርስቲያኖች ሳይሆኑ በልምድ የሚመላለሱትና በንግስና በጥምቀት የሚጋፉቱ ነጠላና ቀሚስ  ለባሾች ናቸው፡፡
         ወንጌልን በትክክል ስናምን በየትኛውም አይነት መንገድ ተሰዳጅ እንጂ አሳዳጅ የመሆን እድል የለንም፡፡ የዛሬዎቹን አብያተ ክርስቲያናት ዘወር ብላችሁ እዩ!!! ከአማኝ ይልቅ እንደ ተሰሎንቄ እብድ አሳዳጅና ደጋፊ ይበዛባቸዋል፡፡ አንድ ክርስቶስ የሞተለት የሥላሴ ሕንፃ ክቡር ሰው በጥንቆላ ፣በዝሙት ፣ በዘፈን ፣ በስካር ፣…ተጠልፎ ወደቀ ተሰነካከለ ሲባል ምንም ትርጉም የማይሰጠው ፤ አንድ ሰው በሰው እጅ የተሰራውን ቤተ መቅደስ (ይበልጣል የምትሉ እንዳትቆጡ!!!)አፈረሰ አቃጠለ ሲባል ግን አንድ ቀን ቤተ ክርስቲያን ያልመጣ ሁሉ ገጀራና ቆመጥ ይዞ ሲፎክር ማየት የተለመደ ነው፡፡በዚያው ትይዩ በሚሸነግል ምላሳቸው ተረትና እውነት ቀላቅለው" የሚያስተማሩ" ለቁጥር የሚታክት ደጋፊ ሲኖራቸው የክርስቶስን ወንጌል በቅንነትና በእውነት የሚያገለግሉ ግን ዛሬም ድረስ ካሉበት አውደ ምህረትና ከሌሉበት አደባባይ እየተገፈተሩ አካላቸው እየደማ ተፈንክተው ሲወርዱና ተሰድበው ሲወገዙም በአይኖቻችን አይተናል፡፡
        ከአፍሪካ በተለይ እኛ ሐገር በሁለት ነገር አዕላፍ ትዕልፊት ደጋፊ ያውም እብድ ደጋፊ ታገኛለህ፡፡ በሐይማኖትና በብሔርተኝነት፡፡ብሔርተኝነት እዚያ ቤተ መንግስት መንደር ብቻ ነው ያለው ብለህ የምትከራከረኝ ጭፍን ተከራካሪ ልትኖር እንደምትችል እገምታለሁ፡፡ግና ልትደርስበት የቀናት ጥናት ይበቃሃል፡፡ በአብያተ ክርስቲያናት ሥር የሰደደ ዘረኝነትን ያለውን ያህል በሌላ ቦታ አለ ብዬ (ከበጣም በጣም ጥቂቶች) ለማሰብ እቸገራለሁ፡፡ ከኢትዮጲያ እስከአሜሪካ ከአሜሪካ እስከ አውሮጳ ባሉት አብያተ ክርስቲያናት የራስን ዘር ፈልጎ ፅዋ መመስረት ፣ዕድር መግባት ፣ጉባኤ መካፈል…እንደ በጎ ሥራ ሲቆጠር ታዝበናል፡፡ ግና በክርስቶስ ደም ከነገድ ከወገን ከቋንቋ ከህዝብ ተዋጅተናል ለማለቱ ምን ብቃት ይኖረን ይሆን?
        በሌላ መልኩ ስለኃይማኖተኝነት ስናነሳ በወረሰው እንጂ ባመነው ኃይማኖቱ የሚኖረው እጅግ ከማነሱም በላይ ኃይማኖቱን የሚኖረው ብዙም አይደመጥም ፤ ቦታም የለውም፡፡ኃይማኖት ከስሜት የዘለለ ልንኖርለትና ልንሞትለት የሚገባ  ነው፡፡ "ቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ የተሰጣቸውን ኃይማኖት ተጋደሉለት" (ይሁዳ.3) ሲባል እንደቅዱስ ጳውሎስ በመገፋትና በመጠላት ብቻ ውስጥ አለፉ ማለት እንጂ ለቅጽበት እንኳ አጸፋዊ ምላሽ መስጠታቸውን ፈጽሞ አንመለከትም፡፡
       የተሰሎንቄ እብዶች ለመልካም ነገር መሸነፍ መቼም አይሆንላቸውም ፡፡ ቃሉን የማሰላሰያና የማጉተምተሚያም ጊዜም የላቸውም፡፡ስለዚህም ስለሃይማኖታቸው መግደልም ካስፈለገ ለእነርሱ ጽድቅ ነውና ከመግደል አይመለሱም፡፡ እንዲህ ያሉትን እብድ ደጋፊ ማፍራት ቀላል ነው፡፡ትውውቅም አያስፈልግም፡፡በሐገራችን ብዙ የእግር ኳስ ደጋፊ እንዳለ እሰማለሁ፡፡"የእኛ" "እኛ" እየተባባሉም እንደሚጠራሩም፡፡ (የሩቅ ማፍቀር ስንችልበት¡¡¡)ታዲያ አንዱ ወገን ከተሸነፈ ድንገት ቢተራረቡ በጩቤ መወጋጋት ጭምር እንዳለም፡፡ (ያልታደልን!!!)
         ወደቤተ ክርስቲያንም ስንመጣ ቲፎዞ ያላቸው ሰባኪዎችና ዘማሪዎች አገልጋዮች እንዳሉ እናያለን፡፡ አለማዊ ልምምዳችን አድጎ ቤተ ክርስቲያናችንን ገዝቷታል፡፡ በትልልቅ ዓለማዊ ስብሰባዎች ላይ እናይ የነበረው በንግግር መሐል ጭብጨባ ዛሬ ከዳር እስከ ዳር እግዚአብሔርን ሳይሆን ስብከት ለማድነቅ ተክነንበታል፡፡ የተሰሎንቄ እብዶች የወንጌል ልብና ጊዜ የላቸውም በእምነት ስም ግን የማሳደድና የመግደል ልብና ጊዜ ተትረፍርፎላቸዋል፡፡
    ኢየሱስን ክርስቶስ ነው ብላችሁ ስታስተምሩ ከሰማው በጣም ጥቂቱ ይረዳችኋል የሚበዛው ግን ድንጋይ ጨብጦ እስከአቴና ድረስ ይከተላችኋል፡፡ ግን እናንተ እውነተኞች ሆይ! ጨክኑ አይዟችሁ፡፡ ከፊታችሁ እነሆ የክብር አክሊል አለና፡፡

               ጸጋ ይብዛላችሁ፡፡አሜን፡፡

13 comments:

  1. God bless you, I really love your article and this blog. God be with you. Please don't stop writing.

    ReplyDelete
  2. Berta tsegawun yabzalh.

    ReplyDelete
  3. Berta wendime geta yebarkih!

    ReplyDelete
  4. Kale hiywet yasemalin.

    ReplyDelete
  5. GOD bless u bro

    ReplyDelete
  6. wendme tebarek melkam yemiyasayuna yeminageru zare tikit nachewna berta.yemtimeleketew melkam newna berta berta berta!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!1

    ReplyDelete
  7. U know why what I like one thing about u?u got the point like I said I never heard about UR blog.I was trying to get something I get hungry &I feel disparate I feel lonely &I'm trying to google it ln different blogs u known I got some but that wasn't makes me strong.finally GOD give me this article thanks for the holly sprit I got relive.oh God bless you bra.I do appreciate your work really I do thanks again keep doing what you doing great job.

    ReplyDelete
  8. አቅሌስያ ዘአማኑኤል26 August 2013 at 05:33

    የጌታ ሥራ የማያልቅ ነው፡፡በምትጽፋቸው ትናንሽ ጽሁፎች በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ አደራ በርታ እንዳታቆመው፡፡በትርፍ ጊዜዬ ሁሉ ደስ እያለን አነበዋለሁ፡፡ጌታ ይባርክህ፡፡

    ReplyDelete
  9. kale hywet yasemaln tsegawn yabzalh wendmachin berta!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  10. God protect you

    ReplyDelete
  11. geta zemenehen ybark berta!

    ReplyDelete
  12. አሜን የኔ ወንድም ተባረክ ፀጋው ከእምነት ጋር ከአንተ ጋር ይሁን

    ReplyDelete