Tuesday 30 July 2013

በናዝሬቱ አለት

Please read in PDF

ጥንቆላና አስማት
መርገምና ምዋርት
ጣኦታትን ማምለክ
መናፍስት ጠሪ

ሰይጣንን አዝማሪ
የአኪጦፌል ምክር
የቃየል ፊት መጥቆር
የአቤሴሎም ብልሀት
የበለአም ስህተት …
     የልጅህን ዓይን በጉጠት ተልትላ
     ለጠላት የምትሸጥ ሸንጋይዋ ደሊላ
     እንደቀይ ዘንዶ ምላሱን አርዝሞ
     ከመንገድ ላይ ቆሞ
     ኢዮብና ኢያሱን
     በበጉ ደም ዛሬም ተዋጅተው ያሉትን
     ከሶ ለማሳጣት
     የሚቸኩለውን የዲያብሎስን ጣት …
የሰዶም አመጻን የቆሬን መቃወም
የሚገዳደርህ ፈርኦናዊውን ሕልም
ከኃጢአት ጋር ኪዳን በደም የተጋቡ
እውነትን ለመቅበር ቀን ከሌ' 'ሚያደቡ …
        በማዕዘኑ ድንጋይ በናዝሬቱ ዐለት
        ይቀጥቀጥ የክፋት የኃጢአት ሠራዊት
        ትውደቅ በላያቸው ታግኛቸው ስምህ
        ይቅለጡ ይብረሱ ነጻ ይውጣ ሕዝብህ፡፡


No comments:

Post a Comment