Tuesday 20 August 2013

ራስን በልክ አለማየት


    የንስሐ ልብ ያለው ተነሳሒ ሰው የመጀመርያ ጠባዩ ራሱን በልኩ ማየቱ ነው፡፡ በየትኛውም ጊዜ ለመጸጸት፣ ይቅርታ ለመጠየቅና በግልጥ ኃጢአቱን ተናዞ ንስሐ ለመግባትም ራሱን ያዘጋጀ ብርቱ ሰው ነው፡፡ በመንፈሳዊውና በዓለማዊው ህይወት ራስን በልክ እንደማወቅ ያለ ታላቅነትና አሸናፊነት ያለ አይመስልኝም፡፡ እንዲህ ያለ ሰው ምን ቢሆን እንደሚሸነፍ ምን ቢያደርግ እንደሚረታ ስለሚያውቅ ተግዳሮትን ማለፍ ድልንም መቀዳጀት ይችልበታል፡፡
         ሁሉን እንደሚችሉ ማሰብና ሁልጊዜ የቀዳሚነቱን ሥፍራ ያለጌታ ለመጨበጥ መቋመጥ ከጎልያዳዊ መንፈስነትና ውድቀት አያዘልልም፡፡ ጎልያድ ምናልባት ቁመቱ ስድስት ጫማ ያህል ሁለንተናው በብረት የተጋጠመና የማይረታ ቢመስልም ልኩ የነበረው ግን መታጠቂያውን በወግ እንኳ ባልታጠቀው በዳዊት ኮሮጆ የነበረችዋ ሚጢጢዬዋ ጠጠር ነበረች፡፡በወንጭፍ ተወንጭፋ ከአናቱ ተሰክታ የጣለችው፡፡

        ትልልቅ የበጎነት ሥራዎች የተሰሩት በትልልቅ ሰዎች ሳይሆን ልካቸውን በሚያውቁበት ትናንሽ እውነተኛ ልቦች ነው፡፡ ተግዳሮቶቻችንና ጠላቶቻችን ከፍ ብለው የታዩን እነርሱ ከእኛ በልጠው ሳይሆን (የተግዳሮት ትንሽ የለውምና) እኛ ያለውን ነገር ገልጠን ማየት አለመጀመራችን ነው፡፡እኛ ያለው ከሁሉ የሚበልጥ ነው ለማለት ራስን በልክ ማየት ያሻል፡፡
       ፋሺስት ኢጣልያ ኢትዮጲያን ሲወር የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ መድፍ ባርኮ ተዋጉበት ብሎ ወደኢትዮጲያ እንደላከ ታዝበን ሳናበቃ ዛሬ እነርሱም በሚያሳፍር ታሪካቸው ሲሸማቀቁ ሲያፍሩበትም እናያለን፡፡ አዎ! ለሚወደን ዳቦ ለሚጠላን መድፍ መባረክ ምን አይነት ጵጵስና ምን አይነት ድንቁርና ይሆን? በምንም አይነት መልኩ ይህንን ግፍ የሚቀበል ህሊናና ልብ አይኖረንም፡፡
           በጥንት ታሪክ እኛም መልካም ገጽታ ነበረን፡፡ የእኛ ወገን ያልሆኑ እንግዶችን በክብር ተቀብለን አስተናግደን፣ ርስት ከፍለን ሰጥተናል፡፡ እንደመታደል ለሚወዱን ብቻ ሳይሆን ለሚጠሉንም የሚተርፍ ሀብትና ልብ ነበረን፡፡ራሳችንን በልኩ እናይ ስለነበር ሌላውን ከመንቀፍ አንደበታችንን ከልክለን በንስሐ ወደፈጣሪ እናነባ መልስም እስከምናገኝ የማንነሳም ነበርን፡፡ ከጥቂት ዘመናት ወዲህ ግን ነገር ተገልብጦብናል፡፡ ከሁሉ በላይ እኛ በሐገራችን ሀብት፣ በኃይማኖታችን፣ በጀግንነታችን፣ በማንነታችንበጣም የተለየን ልዩ ፍጹማን በአለም ላይ እኛንና የእኛን የሚመስል ምንም እንደሌለ ለዘመናት ለፍፈናል፡፡ ያ ሁሉ ልፈፋና ጩኸታችን ግን ምን እንደጨመረልን ሳስብ ይጨንቀኛል፡፡ ራሳችንን በልክ አለማየታችን የንስሐ በር እንኳ ዘግቶብናል፡፡
        አሁን በእኛ ዕድሜ አንድ ሐገረ ስብከት ላይ አንድ "አባት"(በኋላ ጳጳስ የሆኑ) የገዛ የቤተ ክርስቲያን ወገኖቻችንን ከአንዱ ከጌታ እራት የተካፈሉንን ወንድሞችና እህቶቻችንን በድንጋይ እንዲወገሩ ድንጋይ ባርከው የሰጡ አባት እኛም እኮ አሉን፡፡ በባረኩት ድንጋይ እጁ የተሰበረ፣ ዓይኑ የጠፋ፣ አካሉ የጎደለ፣ ሕይወቱ ያለፈዛሬም አሁንም ሕያው ያልሞቱ ምስክሮች አሉ፡፡ (እኛ ላመነው እምነት እንደቅዱሳን እስከሞት በመታገስ ሳይሆን በመግደል እንደምናጸና ካመንን ከምንነቅፋቸው አሕዛብ በምን ነው የተሻልነው? ደግሞስ ይህን ቃየላዊ መንገድ ከየት ተማርነው? ይበልጥ የሚያሳዝነው እንዲህ ያለውን ነውርና ኃጢአት መፈጸሙን አይተን እንኳ ማናችን እንሆን ይህ ልኩን ያለፈ በደል ነው ያልን?)
     ዛሬ የአመለካከት ነጻነት ተከብሯል የሚል አንቀጽ አለም አቀፍ መርህ በሆነበት ዘመን፤ የገዛ ወገንን ያውም ያጠመቁትንና የወለዱትን እንዲህ ማድረግ እንዴት ያለ ድፍረት ነው? ባዶ ትምክህት ተሸክመን ራሳችንን በቅጡ ማየት ተስኖናል፡፡ ለእውነት እየታዘዙ ሐሰትን መጠየፍ ፈጽሞ አልተቻለንም፡፡
     ጉስቁልናችንን፣ ድህነታችንን፣ ራስ ሆነን ወደጅራት መለወጣችን፣ እርቃናችንን መቆማችን፣ ድንግል መሬት እያልን ፎክረን ድንግልናችንን የምዕራባውያን ባህልና የኃጢአት "ቴክኖሎጂ" በየሜዳው የገረሰሱልን፣ ጀግንነት ብለን ለገዛ ስሜታችንና ለአመንዝራነታችን እጅ የሰጠነው፣ የክርስቲያን ደሴት እያልን ትዕልፊት ግብረ ሰዶማውያንን በየጎዳናው ያበቀልነውስላፈሰስነው ደም ለንስሐ መዘግየታችንና ራሳችንንም በልክ አለማየታችንም ነው፡፡
     ራሳችንን ከኃይለኛው በታች ዝቅ ዝቅ አላደረግነውም፣ በቀደመው ዘመንና በአሁኑም "ጠላት" መጥቶብን አይደለም እንደጎርፍ ደም ያፈሰስነው፣አንገት በየጎዳናው የጣልነው፣ ወጣቶችን እንደቅጠል ያረገፍነውበዚህ ሁሉ  ስላፈሰስነው ደምና እንባ ንስሐ ሳንገባ ዛሬም በኃይማኖት ስም ደምና እንባ እናፈሳለን፡፡ የኃጢአት ቀጠሮአችንን ሳንቋጭ "ቅድስት ሐገር " እያልን እንፎክራለን፡፡ ምሕረቱ በዝቶ ዘመን የተጨመረልን ለንስሐ እንጂ ለአመጽ አልነበረም፡፡
   ራሳችንን በልክ እንይ፡፡ ጅራት የሆንነው በኃጠአታችን ነው፡፡ በነገሥታቱ ዘመን ሰላም ሲሆን ጦርነት አምጣ እያልን እጣንና ጧፍ ወደገዳማት እንልክ ነበር፡፡ ይህንንም ነው ታሪክ እያልን በየመዛግብቶቻችን ያሰፈርነው፡፡ ለኢትዮጲያ ሕዳሴ ከልብ ከተጨነቅን ከሁሉ በፊት የሚቀድመው የንስሐ ልብና ብሔራዊ  ይቅርታ እንጂ ያማረ እቅድ፣ ስል ፖለቲከኛና የኃይማኖት ካባ የደረቡ ሰባኪያንና ወንጌላውያንን ማሰልጠን አያዘልቅምና ከሐገር መሪ እስከቤተ ክርስቲያን መሪ፣ ከታላቅ እስከ ታናሹ እንደሞኝ እላለሁ ንስሐ እንግባ፡፡ ከዚህ የባሰም የለምና "የባሰ አታምጣ" ንስሐ አይሆንም፡፡ እጆቻችን ለሁሉን ቻዩ ጌታ ይዘርጉ፡፡
                                ጌታዬ ሆይ! እኔና የአባቴ ቤት በድለናልና ይቅር በለን ፡፡አሜን፡፡





7 comments:

  1. amen Geta hoy yikir belen.

    ReplyDelete
  2. U? Plese verify whose pope did the above and don't generalize hardly
    any sprtiual thought must based on bible word(i dön see any)
    as u are deacon at least u must start with "be semeab we weld..." and end with"we sebhat le egziabher weleweladitu..."
    i have doubt u are same with deacon ashnafi mekonen page(which is kick off by the synod)

    ReplyDelete
  3. በባረኩት ድንጋይ እጁ የተሰበረ ፣አይኑ የጠፋ፣አካሉ የጎደለ፣ህይወቱ ያለፈ … ዛሬም አሁንም ህያው ያልሞቱ ምስክሮች አሉ፡፡ (እኛ ላመነው እምነት እንደቅዱሳን እስከሞት በመታገስ ሳይሆን በመግደል እንደምናጸና ካመንን ከምንነቅፋቸው አህዛብ በምን ነው የተሻልነው? ደግሞስ ይህን ቃየላዊ መንገድ ከየት ተማርነው?

    ReplyDelete
  4. ya hagera sibkat DireDawa nawo.....baergit yasazinal...gin yamininorawo batsatan hulatgna edil mahonun yaminawokawo machie nawo?

    ReplyDelete
  5. Geta hoy bebizu hatiyat teyizenalna yikir belen!!!!!!!!!!!!!! amen.

    ReplyDelete
  6. Shut a heel up you are one of those sacrilegious members PS live theme alone specially this two guys.they stand on their point of view .they are trying to change our dark ideology.i know they are creating a new nation.they goon destroy our generation burden.they goon create 21 century generation.clean in &out they showed as the right path thanks to Almighty God.we cross our fingers all the time.thanks again.

    ReplyDelete
  7. Abetu kekfu hulu adinen tadegenm lezelealemu amen

    ReplyDelete