Friday 25 August 2023

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፩)

 Please read in PDF

ስመ ሥላሴ ለአማኞች የነገር መጀመሪያም፤ የነገር መጨረሻም ነው፤ “በስመ አብ …” ብሎ የጀመረ አማኝ፣ “ስብሐት ለአብ …” ብሎ መጨረሱ እውነትም፤ እምነትም ነው። ለዚህ ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍት ታላቅ ዋቢ፤ ምስክርም ናቸው። “ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።” (2ቆሮ. 1፥2) ብለው ጀምረው፣ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” (2ቆሮ. 13፥14) ብለው መጨረሳቸው እምነትም፤ የእምነታችን ልምድም ነው።

ከዚህም የተነሣ ትምህርተ ሥላሴ የእምነታችን ተቀዳሚና ዋና ትምህርት ነው። እንደ መግቢያ፣ አማኞች ትምህርተ ሥላሴን በትክክል መረዳታችን ምን ይጠቅመናል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚኾኑ፣ ዋና ዋና ምክንያቶችን እንደሚከተለው እናቀርባለን።

1. የሥላሴ ትምህርት መሠረታዊና መኾኑን መረዳት አለብን።

በክርስትና አስተምህሮ ውስጥ በሥላሴ ተጀምሮ፤ በሥላሴ የማያልቅ ምንም ክርስቲያናዊ ትምህርትና ልምምድ የለም። ስሜታችን፣ ልምምዳችን፣ አመለካከታችን፣ ትምህርታችንና መላው አምልኮአችን ከትምህርተ ሥላሴ ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው። ከዚህም የተነሣ በድፍረት እንዲህ ማለት እንችላለን፤ በሥላሴ ትምህርት የማይቃኝ ምንም ክርስቲያናዊ ትምህርትና ልምምድ አይኖርም።

አንድ ሰው ትምህርተ ሥላሴን በትክክል ሳይረዳ ከተበላሸበት፣ ኹሉም ትምህርቱና ልምምዱ ይበላሽበታል፤ ማለትም የተበላሸ ትምህርተ ሥላሴ ያለው ሰው፣ የመዳን ትምህርቱ በምንም መንገድ ጤናማና እውነተኛ ሊኾን አይችልም።

  1. ማወቅ የሚገባንን ወይም የምንማርበትን ዓላማዎች መለየት።

2.1.    ትምህርተ ሥላሴ መሠረት ነው።

አስቀድመን እንደ ተናገርነው፣ ትምህርተ ሥላሴ የክርስትና መሠረተ እምነት ነው። በተለይም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ የተገለጠውን ትምህርተ ሥላሴን መረዳት ዋናና የኹሉ ነገር መሠረት ነው። መጽሐፍ፣ “ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።” (ማቴ. 11፥27) እንዲል፣ የእምነታችን መሠረት ራሱ ትምህርተ ሥላሴ ነው።

2.2.    አለማመንና ማመን ትልቅ ልዩነት ስላለው።

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትምህርተ ሥላሴን ማመንና አለማመን፣ አንዱን አማኝ ሌላውን ደግሞ ኑፋቄ ተከታይ ያስባለ ነውና፣ አማኞች በትክክል ሊያውቁትና ሊያምኑበት ግድ ያስፈልጋቸዋል። አርዮስ በሥላሴ መካከል ያለውን የሥልጣን አንድነት በማበላለጡ፣ በኒቂያ ጉባኤ እንደ ተወገዘ አንስትም፤ ስለዚህ ታሪካችንን ስንፈትሽ ወደ መሠረት ለመመለስና ትክክለኛውን ትምህርተ ሥላሴ ለመረዳት ይጠቅመናል።

2.3.    እውነትን በማወቅ ማደግ ስለምንፈልግ።

 መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ፣ “ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።” (1ጴጥ. 2፥2-3) እንዲል፣ መንፈሳዊ ሕይወት ሕያው ስለኾነ ዘወትር በማደግ ውስጥ ያልፋል። ይህ ግን የሚኾነው ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው፣ “ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ ማስወገድ” ስንችል ብቻ ነው። እነዚህን መርዘኛ ኀጢአተኞች ያላስወገደ ሰው፣ ለመንፈሳዊ ዕድገቱ የሚኾነውን መንፈሳዊውን ወተት መመኘትም ኾነ ማደግ አይችልም።

እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤” (ኤፌ. 4፥15) እንዲልም፣ እኛ ኹላችንም በአካሉ ራስ እየተመራን፣ በአንድነትና ወደ ፍጹምነት ደረጃ እንድናድግ መጽሐፍ ይነግረናል። ክርስቶስ ራሱ ደግሞ እውነት ነው (ዮሐ. 14፥6)፤ እርሱን የላከው እግዚአብሔር አብ ነው፤ (ዮሐ. 3፥34)። መጽሐፍ እንደሚል ኹላችን፣ “እርሱ[አብ] በላከው እንድናምን ነው” (ዮሐ. 6፥29)። አሜን።

“ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ለሚወዱ ኹሉ ጸጋ ይኹን፤ አሜን” (ኤፌ. 6፥24)።

ይቀጥላል …

4 comments:

  1. አብ + ወልድ + መንፈስቅዱስ = እግዚአብሔር = ሥላሴ

    ሥላሴ ወይም Trinity የሚለው፣ ቃል በቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ባይገኝም በትርጉም ግን የእግዚአብሔርን አንድነትና ሦስትነት ለማመልከት የምንጠቀምበት ቃል ነው።
    የይሖዋ ምስክሮች ይህንን አገላለጽ ስለማይቀበሉ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቃሉ አለመገኘቱን አንድ መከራከሪያቸው ያደርጉታል። በብዙ የክርስትና ተከታይ ግን ከላይ በሂሳብ መልክ የቀረበውን ይቀበላሉ።

    ReplyDelete
  2. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  3. BROTHERS, IF DO YOU WANT KNOW REGARDING THE BIBLE,
    1. PRAY TO HOLY GOD
    2. ASK LORD GOD TO KNOW ABOUT HIS WORD TO UNDER STAND.
    3. HOLY SPIRIT WILL SHOW YOU EVERY THING.
    HERE IS THE HOLY TRINITY ON THE BIBLE WRITTEN.
    Mathew 28;17 Therefore go and make disciples of all nations, baptizing them in the name of the Father and the Son and the Holy Spirit.

    Abenezer You are simply a hopeless person. you have been writing many articles criticising our holy church. and to destroy it. but you can't. This great church is based on the blood of GOD, son of the virgin Mary. look how your sister protestant 'churches' are decaying and dying in the west where I am living because their teaching is false and satanic. you are repeating the same false teaching false prophecy. do you know what the end result of all your writing is? it is hell for eternity. becuase your Jesus is not the son of Theotokos but the false mesiah. do u understand ??? you are simply stupid protestant.

    ReplyDelete
  4. God bless you! Biblical content,

    ReplyDelete