Monday 21 December 2020

“ዲያቆን” ሄኖክ ሃይሌና አዲሱ ኑፋቄው!

 Please read in PDF

“እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን መሥራት ትችላለች” [እውነት?!]

“ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።” (1ቆሮ. 3፥17)

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ መናገር ኑፋቄነት፣ ቅዱስ ቃሉ የማይለውን መናገር ደግሞ አማኝነት ወይም “የቤት ልጅ” የሚያስብለው ተግባር ከኖረ ሰነባበተ። ለቅዱሳን መላእክትም ኾኑ ሰዎች፣ “ቃሉ ከተናገረው በላይ መናገር ትክክል አይደለም፣ የተነገረው ብቻ ሊነገርላቸው ይገባል” ስንል፣ “ጸረ ቅዱሳን፣ ጸረ ማርያም፣ ጸረ መላእክት …” የሚል ስድብ ያስቀጥላል። ነገር ግን ለቅዱሳን፣ ቅዱስ ቃሉ የሚናገረውን ብቻ አለመናገር የቅዱሳኑ ጠላቶች መኾናቸውን በቅዱስ ቃሉ ላይ ጨምረው ተናጋሪዎቹ ያስተዋሉ አይመስሉም።



“ዲያቆን” ሄኖክ ሃይሌ አንድ ቃለ መጠይቅ አድርጐ ሰማኹት፤ ቃለ መጠይቁ አንዳንድ መራራ እውነቶች አሉት፤ ከመራራ እውነቶቹ ጥቂቱ!

·        “ኢየሱስ ብቻ ሲባል የሚከፋቸው ካሉ የአረዳድ ችግር ነው። ኢየሱስ ማለት መናፍቅነት አይደለም። ስሙ ሲጠራ የሚደነግጥ ችግር ያለበት ነው።” ይህን የተናገረው ሄኖክ ነው። አስተውሉ! “ኢየሱስ ብቻ ብሎ መጥራት የመናፍቃን መለያ ነው” ለዓመታት ተብሎአል፣ “እንደ ጋለሞታ እንዴት ያለ ማዕረግ ትጠሩታላችሁ? ባልዲና ማንቆርቆሪያ እንኳ ማንጠልጠያ አለው፣ ኢየሱስን እንዴት ከባልዲና ከማንቈርቆሪያ ታሳንሱታላችሁ” ተደጋግሞ ተብሎአል። ነገር ግን ዛሬ ነገር ተለወጠ፣ እንዲህ ማለታቸው በእውነት ለራሳቸው ተከታዮች መራራ እውነት ነው። በርግጥ ባልዲና ማንቆርቆሪያ ጥገኞች ናቸው፣ ኢየሱስ ግን ዘላለማዊና ኢ ጥገኛ ነው ብንልም በጊዜው ማን ሰምቶን?!

·        “አሥርቱ ትእዛዛት የተጻፈበት ታቦት የለም!” ይህንም ያለው ሄኖክ ነው። እንኪያስ የቅዱሳን ምስል የተቀረጸበት ታቦት ከወዴት ተገኘ? ሙሴ እንኳ በብሉይ ኪዳን ሥራ የተባለው ታቦት፣ “ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።” (ዘጸ. 34፥1) ነው። “እንደ ፊተኞቹ” ማለት ሕግና ሥርዓቱ እንደ ተጻፈባቸው ማለት ነው (ዘጸ. 32፥15)፤ ነገር ግን አሥርቱ ትእዛዛት የተጻፈበት ታቦት ከሌለ፣ ሌላው ከወዴት መጣ?! መቼም መንፈስ ቅዱስ አንደበት አጽፍቶ እውነት ያናግራል ማለት እንዲህም አይደል?!  

አስቂና አዲሱ የሄኖክ ኑፋቄ!

·        ጠያቂው ስለ ማርያም ምልጃ ሲጠይቀው፦ ሄኖክ፣ “ማርያምን ኢየሱስ ራሱ ለምኖአታል” ብሎ ይመልስለታል። አዲሱ ኑፋቄውንም እንዲህ በማለት ይቀጥላል፣ “እመቤታችን ማማለድ አይደለም አፍርሳን ልትሠራን ትችላለች።… ኢየሱስ ራሱ ሲጨንቀው ወደ እርሷ ይሄድ ነበር። እጆቹን ይዛ ሲድህ መርታዋለች። እኛም እንድትመራን ወደ እርሷ እንማጸናለን” ይላል። በመቀጠልም የሰሎሞን እናት ሰሎሞንን ስትለምን “የፈለግሽውን ጠይቂኝ” እንዳለ፣ እንዲሁ ኢየሱስ ከሰሎሞን ይበልጣልና ማርያምም ከሰሎሞን እናት ትበልጣለች በማለት የማርያምን አማላጅነት ከምድራውያን ነገሥታት መሪዎችና እናቶቻው ጋር ለማነጻጸር ይጥራል።

 ሄኖክ ኃይሌ፣ ለምልጃ ትምህርት ይህን ያህል ሩቅ መኾኑ፣ ኢየሱስ በናዝሬት ሰዎች አለማመን እንደ ተደነቀው ያስደንቃል። ምልጃ መሠረታዊ ትርጕሙ አንዱ ስለ ሌላው መለመን ነው። ማርያም፣ መላእክት፣ ሌሎች ቅዱሳን ሰዎች አያማልዱም፣ መለመን አይችሉም የተባለው፣ በቦታና በጊዜ የሚገደቡ ስለ ኾኑ፣ ሞት ስለሚገዛቸውና በዚህ ምድር ያለውን መላውን ነገር ስለማያውቁ ወይም ምሉእ በኵለሔ ስላይደሉ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ በአዲስ ኪዳን ዋና ሊቀ ካህናት አንድ ብቻ፣ እርሱም መሲሑ ኢየሱስ መኾኑንና በእርሱም ካልኾነ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚቻለው እንደ ሌለ በግልጥ ይናገራል። ክርስቶስ ብቸኛ መካከለኛ፣ ብቸኛ ሊቀ ካህናት፣ ብቻውን ብቃት ያለውን መሥዋዕት ያቀረበና መላውን ዓለም ከራሱ፣ ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያስታረቀና የሚያስታርቅም ነው። ይህ አስደናቂ አለ መኾኑን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ “ቀድሞ ሊቀ ካህናት ይለምን እንደ ነበረ ዛሬስ ለለመነ አምላክ ይለምናል ብለህ አታድንቅ። ሊቀ ካህናት እንደ መኾኑ ስለ ለመነ አታድንቅ። … ስለ ምን ሰው ኾነ ሰው ካልሆነ አያድንምን የሚል ሰው ቢኖር አዎን ሰው ካልኾነ አያድንም ብለን እንመልስለታለን። (ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ። 17ኛ ድርሳን ቁ. 31-37 ገጽ 302) ፡

እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድም ቦታ ኢየሱስ ማርያምን ሲጨንቀው የለመነበት ቦታ የለም፤ ጌታ ኢየሱስ በኖረበት ዘመኑ ኹሉ የለመነውና የጸለየው አባቱ አብን ብቻ ነው። “የላከኝም ከእኔ ጋር ነው፤ እኔ ደስ የሚያሰኘውን ዘወትር አደርጋለሁና አብ ብቻዬን አይተወኝም” (ዮሐ. 8፥29 በተጨማሪም 8፥16፤ 16፥32 ይመ.) እንዲል። አብ በልጁ መሥዋዕት ረክቶአል፤ ስለ መዳናችን ከኢየሱስ የተሻለ ምልጃ፣ መሥዋዕት፣ አስታራቂነት፣ ቤዛነት … ያቀረበ፤ ሊያቀርብልንም የሚችል በሰማይም፤ በምድርም ማንም የለም። ይህን ትምህርት ለመቃወም ግን ማርያምን በግድ ወደ ኢየሱስ ማስጠጋት፤ ማተካከል ማርያምን መጥላት እንጂ መውደድም፤ ማክበርም አይደለም። ደፍረን ግን እንዲህ እንላለን፤ “መዳንም በሌላ[ከኢየሱስ በቀር] በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (ሐዋ. 4፥12) አሜን።

 

25 comments:

  1. "ወስሉጥ ስምኪ በኀበ እግዚአብሔር" ተብሎ የተነገረላት ወላዲተ አምላክ አሁንም አፍርሳ መስራት ትችላለች። ካልገባህ ዝምምም!

    ReplyDelete
  2. ወዳጀ በራሳችሁ መቆም አትችሉም እኮ እናንተ ክርስቶስን የሰበካችሁ የሚመስላችሁ የሌላውን አስተምህሮ ስትተቹ በተንሻፈፈ መነፅራችሁ ስታብጠለጥሉ ነው እኔ ልንገርህ ዳቆን ሄኖክ ሃይሌ አንተን አፍርሶ ይሰራሀል ለዚህ ምን ትላለህ በመጀመሪያ እንደየ ስሜታችሁ ከመኖር ውጡና የምትመሩበት ማንዋል ይኑራችሁ ከሌላው የምትለዩበት ድንበር ይኑራችሁ ሌላውን መክሰስ ላይ አትጠመዱ

    ReplyDelete
    Replies
    1. እኛ የምንኖርበት ማንዋል መፅሐፍ ቅዱስ ይባላል። እርሱ ደሞ እውነት ከመናገር ወደ ዋላ ብሎ አያቅም።

      Delete
  3. አርዮስም ክህደቱ እንዳንተው ነበር አውቄአለሁ መጥቄ አለሁ ሲዘላብድ የነበረው አዎ አንተ ደግሞ ከአርዮስ የከፋህ ሰርጎ ገብ የወያኔ መልእክተኛ የጥልቁ ልጁ መሆንህን እራስ አየመሰከርክ ነው ብዙ ማውራት መሰንጠቅ መተርተር ከጥልቁ ተምራችኋል ኧረ መሬት ሰንጥቃችሁ ውቅያኖስ ከፍላችሁ በአየር ቀዝፋችሁ ብርሃን በብርሃን ተጥለቅልቃችሁ ብርሃን መስላችሁ እንደ ምትከሰቱ አስቀድሞ ተነግሯል አታስደነግጡም አታስደንቁም

    ReplyDelete
  4. ተሀድሶ ነህ።

    ReplyDelete
  5. ምን አይነት የተረት አባት ነክ እስቲ እናትክን እፃን እያለሁ ምን ምን እል ነበረ ብለክ ጠይቅ ???

    ReplyDelete
  6. ቤ/ክ ልታወግዘው ይገባል። ይህ ከአሪዮስ በምን ይተናነሳል!

    ReplyDelete
  7. አፍራሽና ሰሪ ያደርጓቷል እንደፈለጉ ነው እነሱ ቤት

    ReplyDelete
  8. መናፍቅስ አንተ
    ጫፍ እየያዛችሁ ምትሮጡ
    የአርዮስ ሽንቶች
    መጀመሪያ በስርአት አዳምጡ

    ReplyDelete
  9. ጌታችን ልጅ ሳለ እንደ ህጻናት ከእናቱ ጡት ለምኖ መጥባቱን አታውቅማ ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. አሀ እሱን ነዋ ሲጨንቀው የለመናት.... አረ አታስቁን ወንድሞቻችን

      Delete
  10. ጥቅስን ያለ ቦታው መደንቀር በራሱ ኑፋቄ ነው በእርግጥም ፈርሰው መሰራት ከሚገባቸው ቀሳጥያን አንዱ አንተ ነህ!

    ReplyDelete
  11. እመቤታችን ስም ሲጠራ ምድረ ግሪሳ አረፋ መድፈቅ ትጀምሪያለሽ።

    ReplyDelete
  12. ለዚያውም አፍርሳ ብትሰራን የምንወዳትን እኛን እንጂ አንተን አይመለከትም!! አይዞህ ለማንኛውም ብሉይኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ጥላ/ ምሳሌ ነው ጳውሎስን ስማው በመልክቱ።ሌላው ግርም የሚለኝ ለእየሱስ ክሮስቶስ ብቸኛ ተቆርቋሪ ነኝ አልክሳ ማርያም ያላዘለችው፣እጁን ይዛ ያልመራችው እየሱስ እራሱ እየሱስ አያውቀውም

    ReplyDelete
  13. በጣም ይገርማል ቅዱሳንን ሞት ይወስናቸዋልክ ማለት መፅሐፍ ቅዱስን አንተ የሚመችህን ብቻ ነው የምታነበው ማለት ነው እኔ የአብርሃም የይሳቅ የያእቆብ አምላክ ነኝ የህያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለሁም ማቴ ; 22
    ዲ/ ን ሄኖክን አይደለም መተቸት ተማሪው ለመሆን አቅሙ የለህም

    ReplyDelete
  14. ዝም በል ባክህ አንተ መናፍቅ።

    ReplyDelete
  15. በትክክል ተባርከሀል

    ReplyDelete
  16. እራስህን ለካህን አስመርምር

    ReplyDelete
  17. ጠማማ ልብ ያለዉ መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል። ምሳ 17÷20 እንዲል መጽሐፍ ልብህ ጠማማ ከሆነ ነገሮችን በቀላሉ ልትረዳ አትችልም። በወንጌል ደግሞ ለመረጣቸዉ አጋንንትን እዲያወጡ፣ሙት እንዲያነሱ፣ ሽባ እንዲተረትሩ፣ ድዊ እንዲፈውሱ ማቴ 10÷8 አልፎም በእርሱ ለሚታመኑ እርሱ ካደረገዉ በላይ እንደሚያደርጉ የፍጥረታት ጌታ ሁሉ በእርሱ የሆነ መድህነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በማይታበል ቃሉ ተናግሯል። ዮሐ 14÷12
    በመሰለህ አትጓዝ ማስተዋሉን ያድልህ።

    ReplyDelete
  18. ጠማማ ልብ ያለዉ መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል። ምሳ 17÷20 እንዲል መጽሐፍ ልብህ ጠማማ ከሆነ ነገሮችን በቀላሉ ልትረዳ አትችልም። በወንጌል ደግሞ ለመረጣቸዉ አጋንንትን እዲያወጡ፣ሙት እንዲያነሱ፣ ሽባ እንዲተረትሩ፣ ድዊ እንዲፈውሱ ማቴ 10÷8 አልፎም በእርሱ ለሚታመኑ እርሱ ካደረገዉ በላይ እንደሚያደርጉ የፍጥረታት ጌታ ሁሉ በእርሱ የሆነ መድህነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በማይታበል ቃሉ ተናግሯል። ዮሐ 14÷12
    በመሰለህ አትጓዝ ማስተዋሉን ያድልህ።

    ReplyDelete
  19. መናፍቅስ አንተ
    ጫፍ እየያዛችሁ ምትሮጡ
    የአርዮስ ሽንቶች
    መጀመሪያ በስርአት አዳምጡ

    ReplyDelete
  20. Ante menew tekorkuwari negn alk.degmom egna Orthodoxoch out of Biblen seleminamn lenastemerm hone lenesbk enchelalen'''Awald mesahft....

    ReplyDelete
  21. በጣም ያሳዝናል እኔ የምሰጋው ይሄ ነገር እያደገ እያደገ ሄዶ ፈጣሪያችን ናት እንዳይሉ ብቻ ነው !!!
    እኛ እንወዳታለን ብፅእት ናት ከሴቶች ተለይታ የተባከች ናት ቃሉ እንደሚለው መጽሀፍ ቅዱስ የማይለውን ነገር ማንም ቢሰብክ ስህተት ነው ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ ታሳፍራለህ

    ReplyDelete
  22. ምን እርስ በርስ ያባላችዃል

    ReplyDelete
  23. ዲያቆን ሔኖክ ሊል የፈለገው ነገር ባልተገባ መንገድ ተተርጉሟል ።

    ReplyDelete