Wednesday 9 December 2020

ላ’ንዱ የ’ኔ ቢጤ

Please read in PDF

   ጥንት  እንደ ሰማነው በቃየል እጀታ

   በኋላኛው ዘመን በኢየሱስ ጌታ

   ያቺ አመንዝራ ተከሳ ስትመጣ 

   ድንጋይ ጨብጠዋል ቀን ሊያሳጥሩ

   የእፉኝት ልጆች ሞትን ሊሸልሙ።

        ድንጋይ ቤታቸውን በዘብ አስጠብቀው

        የሥላሴን ቤት ግን ሲያፈርሱ ተባብረው

        ምነው የኀጢአት ጡት ከሚመገምጉ

        አምሳለ ሥላሴ ሰው ከሚያሳድዱ …

        ለመግደል በያዙት በዚያው በድንጋዩ

        ካብን ክበውለት ላ’ንዱ የ’ኔ ቢጤ ጎጆ ቢቀልሱ?!

 

(2005 ዓ.ም ተጻፈ፤ ሐረርጌ - ጃርሶ አሌ)

 

1 comment:

  1. ተስፋችን በሆነው በጌታ በየሱስ ክርስቶስ አሁንም እናመሰግናለን እርሱ በዙፋኑ ላይ ነው እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ

    ReplyDelete