Monday, 14 December 2020

“ዘማሪት” ትርሃስና “ወደ ኋላ አልልም ከእንግዲህ” የሚለው መዝሙሯ!

 Please read in PDF

“አልወጣሁም እያልሽኝ ነው፤ … እያልሽ ያለው ነገር ግን እየተዋጠልኝ አይደለም፤ እየተቀበልኹትም አይደለም … ” ይህን የተናገረው ቃለ መጠይቅ ያደረገላት ልጅ ነው፤ ጌታ ኢየሱስን የሚያፍሩበት ኹሉ እንዲህ ሊዋረዱና ሊያፍሩ ይገባቸዋል! በልጁ የሚያፍር፣ በምድር ማንም ባያምነውና “ንግግርህ አይዋጥልኝም” ቢለው ትክክል ነው፤ ትርሃስ እንዲህ ስትባይ ምን ተሰምቶሽ ይኾን? በኢየሱስ አፍረሽ ማን እንዲመሰክርልሽ ወደሽ ነበር?!


እንዲህ ዘምራ ነበር!

 “ወደ ኋላ አልልም ከእንግዲህ

ስላየሁህ ፊቴ ተስለህ

ከተገለጥክልኝ ሕያው ተድላ

አልሻም በጭራሽ ካንተ ሌላ።

… የማልሸቅጥብህ ንዑድ ጌታ

የማልደርብብህ ንጹህ በፍታ።

አንተን ያሉትን በጽኑ ስከስ

መች ተጸየፍከኝ በዕንባ ስመለስ

ደማስቆ ሳልደርስ ደርስህልኝ

የጽድቅህን ጦር አስታጠቅኸኝ”

ይህን መዝሙር ዘምራ ነበር፤ አዎን ዘምራ ነበር!

የኋሊት እንሽርት!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከ“ሐዳስያን ጋር እያገለገልን ነበር፤ አኹን ግን ትምህርታቸውና ሕይወታቸው ትክክል አይደለምና ከእነርሱ ተለይተናል ወይም ደግሞ ጨርሶ ከእነርሱ ጋር አልነበርንም” የሚሉ ዘማርያንና ሰባክያንን እየሰማን ነው። ከእነዚህ ውስጥ አንዷ ደግሞ ከሰሞኑ ትርሃስ ገብረ እግዚአብሔር ኾና መጥታለች። “አብሬ አገለገልኩ እንጂ አብሬአቸው አልነበርኩም” ስትልም አብረዋት የነበሩትንና “ዝማሬ የሰጧትን” ወንድሞችና እህቶችን ሽምጥጥ አድርጋ ክዳለች። እንዲህ ማድረግ ግን ለምን ፈለገች?[ሌሎችስ ለምን ይህን መንገድ ይከተላሉ?] ብዬ ብጠይቅ፣ ጎልቶ የሚሰማኝ ድምጽ አንድና አንድ ብቻ ነው። በስሙ ያፍራሉ። አንዳንዶች፣ ልብስ፣ እንጀራ፣ መኖሪያ፣  የአውሮፓና የአሜሪካ መኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት፣ የገንዘብ እጦት፣ ራብና ጥምን መታገሥ አለመቻል፣ የትዳር ዋስትና ስለሌላቸው … ሊሉ ይችላሉ፤ ግን በስሙ ያመነና የማያፍር አማኝ የቱንም መከራ ይታገሣል፤ ነገር ግን ኹላቸውን ይህን አይወዱም፤ ምን ብንል?

በስሙ መከራ መቀበልን አይፈልጉም፦ ወደ ኋላ የሚንሸራተቱ ኹሉም አገልጋዮች ቀዳሚ ነገራቸው በማርያም ስም እንጂ በኢየሱስ ስም መከራ መቀበል አይፈልጉም። በኢየሱስ ሲታሙ ያፍራሉ፣ በማርያም ስም ግን ማናቸውንም ነገር ደፍረው ይናገራሉ፤ ሲዘምሩም አያፍሩም። በኢየሱስ ግን ይሸማቀቃሉ፤ አንገት ይደፋሉ። የሚዘምሩት የተሰጣቸውን እንጂ ያመኑበትንና የሚኖሩትን አለመኾኑን መመለሳቸው ይመሰክራል!

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ቃል መከራንና ነቀፋን ኹሉ መቀበል ያለብን በኢየሱስ ስም መኾኑን እንዲህ ይናገራል፣ “ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።” (ማቴ. 5፥11)፣ “ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ።” (ሉቃ. 6፥22)፣ “እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው እንደ ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ። ዳሩ ግን የላከኝን አያውቁምና ይህን ሁሉ ስለ ስሜ ያደርጉባችኋል።” (ዮሐ. 15፥20-21)፣ “ሐዋርያትንም ወደ እነርሱ ጠርተው ገረፉአቸው፥ በኢየሱስም ስም እንዳይናገሩ አዝዘው ፈቱአቸው። እነርሱም ስለ ስሙ ይናቁ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ ከሸንጎው ፊት ደስ እያላቸው ወጡ፤ …” (ሐዋ. 5፥41)።

“ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ።” (ማቴ. 10፥32-33)

“ወደ ኋላ አልልም” ብላ ብትዘምርም፣ ወደ ኋላ በመመለስ ልክፍት ተይዛለች፤ የኋሊትም ሸምጥጣ ተመልሳለች፤ ነገር ግን ትርሃስም ኾነች ሌሎችን እንዲህ እንላለን፤ በስሙ መከራ መቀበልን የምታፍሩ ሆይ፤ መንገደኛ ኹሉ እንደሚያሳፍራችሁ፤ እንደሚያዋርዳችሁ፤ ይህን እውነት ደፍሬ እናገራለሁ። ጌታ ግን በታማኝነቱ በዙፋኑ አለ፤ እስከ መጨረሻ ለሚጸኑት አክሊልና ሕይወትን ይሸልማል፤ አሜን።


15 comments:

  1. ቀን ሳለልህ ተመለስ አለበለዚያ ግን ይነጥቅሃል በአንተ ቤት ስለ እዉነት ሐስክረሃል ግን ሞተሀል አንተ ግብዝ ሰዉን ከምትዘልፍ ወደ ንሰሐ ተመለስ ከአርዮሳዊና ከነሰባሊዮስ የክህደት ትምህርት ተመለስ

    ReplyDelete
  2. ዝም ቢሉ ምና አለ? ሲጀመርም የመዳን ነገር ገብቷቸዋልወይ?? የሚዘምሩት እኮ አየሩን አይተው ነው፡፡

    ReplyDelete
  3. የፈራ ይመለስ

    ReplyDelete
  4. Ketemelesech eseyew kehedechim mebtua new.... yekal meteyku mels gn????

    ReplyDelete
  5. ጥቅም ፈላጊዎች ምድረ ሆድ አደር የይሁዳ ልጆች ። ። በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ስም የምትነግዱ ተኩላዎች ! ለማያዉቃችሁ ታጠኑ ። ሁላችሁም ። 🤔🤔 ዘማሪ ነች ተብዮም ፖሳቹም ሼር አድራጊዉም ። ። ኧጭ አበዛችሁት አሁንስ አይን ከማዉጣታችሁ ! ከተዋሕዶ እራስ አትወርዱም ። ተዉን !!!

    ReplyDelete
  6. ሲጀመር ጌታን አላወቀችውም፣ ድነትም አልገባትም፡፡ እኔ ስለነዚህ "አገልጋዮች" ሳስብ በደንብ ሳይማሩ ሳይለወጡ መድረክ ስለለመዱ ብቻ ወዲያው "አገልግሎት" እየቀጠሉ ነው፡፡ ስለዚህ ከአገልግሎት በፊት መለወጣቸው ይፈተሽ እላለሁ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. አንቺ አውቀሽ ሞተሻል:: እኔ እኮ በቃ ግርም ነው ምትሉኝ:: ከእናንተ ጋር ሆኖ ምንም ይሁን ምን ብቻ ጌታ ጌታ ካለ ፃድቅ ነው:: አይ የለም ይህ መስመር ትክክል አይደለም:: ዕውነት የለበትም ብሎ መርምሮ ከዛ እግዚአብሔር ሲመልሰውና በትክክለኛ መስመር ሲመራው አይ ትክክል አይደለህም ብሎ ውርጅብኝ ማውረድና መተቸት... ከጁንታው እኔ ብቻ ሃገርን ልግዛ ከሚል አስተሳሰብ አይተናነስም:: ከንቱዎች ናችሁ:: በዚህ ባለቀ ዘመናችን የትንቢት መፈፀሚያ እንዳትሆኑ እግዚአብሔር ልቡና ይስጣችሁ ብቻ::

      Delete
    2. 1ኛ ቆሮንቶስ 1
      ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
      ❝²² መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥
      ²³ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
      ²⁴ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።
      ²⁵ ከሰው ይልቅ የእግዚአብሔር ሞኝነት ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።❞

      Delete
    3. ይኸውልሽ ከአንቺ በላይ ጥቅስ መጥቀስ የምችል ሰው ነኝ :: ጥቅስ በመጥቀስ ብቻ ጉንጭ አልፋ ንትርክ ማድረግ አልፈልግም:: ጥቁሱንማ አጋንንትም ይጠቅሱታል:: እሱ አይደለም ቁም ነገሩ እህቴ::
      ትርሃስን ካንቺ በፊት ጠንቅቄ አውቃታለሁ ተመለሰች ቢሉኝም ብዙም ያልደነቀኝ ሰው ነኝ:: አንቺም ትላትና በቅጡ ባልተረዳሽው የሉተር ትርክት ጌታን አውቀሽ ሞተሽ ትርሃስን ሲጀመር ጌታን አላወቀችሁም ትያለሽ?? ሲጀመር የምታውቀውን ጌታዋን ነው አሁንም የያዘችው:: ላንቺ መማር መለወጥ ጌታ ጌታ ማለት ከሆነ መድረካችሁ እንኳንም ቀረባት ባፍንጫዋ ይውጣ::

      Delete
  7. የማርያም ሆነች ማለት የኢየሱስ አይደለችም ማለት ነው?😌

    ReplyDelete
  8. እሺ አቤነዘር ተኩላው እና የነ በጋሻው ዕቃ ትርሃስ

    ReplyDelete
  9. She was right on right please God bless my dear sister

    ReplyDelete
  10. እኛ ሠዋች የምንባል ግን ለምንድን ነው የሰወችን ነብስ የምናስጨንቀው ፕሮግራሙን ተከታትየዋለው ። ልጅቷ በትክክለኛው መንገድ ለማስረዳት ሞክራለች እና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጅ ነኝ ብላለች ይህንንም ደግሞ እሷ እና አምላክ ብቻ ነው የሚያውቁት ታዲያ አኛ ማን ሆነን ነው ፈራጅ የምንሆነው ።ለሁላችንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን ።እህታችንንም በሃይማነኖቷ ያጠንክርልን።

    ReplyDelete
  11. አናስተባብልም አይደለንም ብለን፣
    አዎ የኢየሱስ ነን መዳን ተቀብለን ፣
    ከእንግዲህ ምን ቀርቶን እንሸቃቅጣለን፣
    ኢየሱስ ጌታ ነው እያልን እንሞታለን ።

    ReplyDelete
    Replies
    1. Woow yeberallnin ewunet aminen semay engeballen

      Delete