Wednesday, 7 October 2020

የልጁን መልክ መምሰል (ክፍል ፫)

Please read in PDF

እንዲህ ነበርን!

ካለፈው የቀጠለ...

5. በአሳባችን ጠላቶች ነበርን፦ ኹላችን በእግዚአብሔር ፊት፣ “… ክፉ ሥራንም በማድረግ በአሳባችን ጠላቶች ነበርን” (ቈላ.1፥21-22)፡፡ እጅግ ክፉዎች ከመኾናችን የተነሣ በእእምሮአችንና በልባችን ለራሳችን የምናዳላ ራስ ወዳዶች ነበርን፡፡ በምድር ላይ አንድም መልካም ሰው መገኘት እስከማይችል ድረስ ኹላችንም ለእግዚአብሔር ጠላቶች ነበርን፡፡

ዝንባሌአችንም አንዳች መልካም ነገርን ማመንጨት የማይችል ደካማና ክፉ ነበር፡፡ ሰይጣን እንደ አሻንጉሊት ሲጫወትብን እኛ ኹላችን በዐሳባችን የሰይጣንን ፈቃድ እንፈጽም ዘንድ ባሮችና ለእግዚአብሔር ከቶውንም የማንመች ጠላቶች ነበርን፡፡ ጳውሎስ ይህን በብዙ መንገድ አስፍቶና አምልቶ ሲናገር እናስተውለዋለን፤ “ገና ደካሞች ሳለን … ገና ኃጢአተኞች ሳለን … ጠላቶች ሳለን” (ሮሜ 5፥6፡ 8፡ 10) በማለት በክፋት እንዴት ጸንተን እንደ ነበርን አስረግጦ ይናገራል፡:

6. ወገን፤ ምሕረትም ያገኘን አልነበርንም፦ “እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም … እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም” (1ጴጥ. 2፥10) እንኪያስ ምን ነበርን? ብለን ብንጠይቅ፣ “ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።” እንዲሁም፣ “አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ ነበርን” (ኤፌ. 2፥3፡ 11)፡፡ ከዚህም የተነሣ ከእግዚአብሔር ዘንድ በኀጢአታችን ምክንያት እጅግ ርቀን ነበርን፡፡

   ከኪዳኑ ያፈነግጥን፣ ባለመታዘዝ የጸናን፣ የገዛ መንገዳችንን ተከትለን እንደ በጐች የተቅበዘበዝን፣ ያገኘን ጠላት ኹሉ የነዳን፣ ለተገዛንለትም ኹሉ ባሮች ኾነን እጅግ ምስኪኖች ነበርን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከትልቅ ፍቅርና ምሕረቱ የተነሣ ኹላችንን ያድነን ዘንድ እንዲሁ ወደደ፤ ፈቀደም፡፡

ይህን ስንል በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የሚያድንና የሚታደግ አምላክ ሆኖ አልተገለጠም ማለት አይደለም። እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳንም የኪዳኑን ሕዝብ በብዙ ታድጐ ጠብቋል (ዘዳግ. 26፥8፤ መዝ. 27፥1፤ 88፥1) ፤ ነገር ግን ፍጹም የሆነውን መዳን በሰው ልጅ ያደረገው በክርስቶስ ኢየሱስ ላመኑትና ለተቀበሉት ሁሉ ነው። በእርግጥም ምንም እንኳ ይህን ሁሉ የነበርን፤ በድቅድቅ ጨለማ እንደሚኖር ሰው ፈጽሞ ከየት ወደየት እንደምንሄድ ሳናውቅ በብዙ ጥፋት ስንኖር የነበርን ብንሖንም በምሕረቱ ባዕለጠጋ የሆነው ጌታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ ያመንነውን ልጆቹን፦

1.      ርስቶስ ኢየሱስ የሞትን ኃይል አስወግዶ የሕይወት ኃይል ሰጠን ፤ አጠበን ፤ ቀደሰን ፤ አጸደቀንም (1ቆሮ. 6፥9)። ይህን ልብን የሚመላ፤ አዕምሮን የሚያልፍ ድንቅ ነገር ነው! ይህንን ጽድቅ፤ ቅድስናና ንጽሕና የምናገኘነው ወይም የሚሰጠን በክርስቶስ ኢየሱስ (ሮሜ.3፥24) ሲሆን፥ ይኸውም በሞቱና (ሮሜ 3፥25፤ 5፥8) በትንሣኤው (ሮሜ 5፥10) እንዲሁም ዘወትር ትኩስ ሆኖ ዛሬም ድረስ በሚታይልን (ዕብ.9፥24)፥ ከአቤል ደም ይልቅ የተሸለውን በሚናገርልን (ዕብ. 12፥24) በደሙ ኃይል ነው።

2.      ጌታ ብርሃን ሆንን፦ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ”፤ “አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ” (ማቴ. 5፥14 ፤ ኤፌ. 5፥8) ብርሃኑ በሕይዋተችን ብቻ ያበራ አይደለም ፤ ጨለማ ለወረሰው ለአሮጌው ሰው ጠባይ ሁሉ የምንታይና በዝምታ የምንወቅስ በማድረግ ነው፤ ብርሃን እንድንሆን የወደደው (ማቴ. 5፥14) ብርሃኑ በእርሱ ዘንድ ያለማንነት እንጂ ከእኛ የሚመነጭ አይደለም። ብርሃኑ ከእርሱ ለእኛ የሆነልን ስለሆነ ክብሩና ውዳሴው ለእርሱ  ብቻ ነው። “የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል” (ራእ. 5፥12) እንዲል።

3.      ክርስቶስ ደም የቀረብን ሆንን (ኤፌ. 2፥13)፦ የገዛ መንገዳችንን ተከትለን ከክርስቶስ ብንርቅ፤ ራሱ ክርስቶስ በደሙ ቀረበን፤ አቀረበንም። ይኸውም “እንደእግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኃጢአት ይቅርታ” ባገኘንበት ሞቱ ነው (ኤፌ. 1፥7) በመከራውና በሞቱ የፈሰሰው ደም ለኃጢአተኞች ሁሉ የተከፈለ ውድ ዋጋ ሆኖ ማንም ወደማይቀርበው ወደ እግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ በኩል ለመቅረብ በቃን።

    ከክርስቶስ የራቅን ሁላችን መቅረቢያችን ራሱ ክርስቶስ ብቻ ነው። መራቅ የቀደመ ሥፍራን ሙሉ ለሙሉ መልቀቅን ያመላክታል። በእግዚአብሔር ገነት የነበረንን ሥፍራ በሰይጣን ምክር ተታልለን ፤ በገዛ ፈቃዳችን ትተን ከእግዚአብሔር ፊት ኰብልለን ወጣን፤ ራቅንም (ዘፍ. 3፥8፤ 24) በክርስቶስ ቀረብን ስንል ያንን በእግዚአብሔር መልክ ልንኖርበት የሚገባውንና የሚልቀውን ክብርና ሞገስ በእርሱ ክብርን ሁሉ ወርሰን ቀርበናል ማለታችን ነው።

4.      ለ ክርስቶስ የነበርነውን ሁላችን በእርሱ በክርስቶስ፤ ለክርስቶስ ሆንን፦ አባት የሚወደው ልጅ ከባድ ወንጀል ቢሠራበት፤ ስለልጁ ፈንታ ጥፋቱን አምኖ በመቀጣትና በመካስ ልጁን ነጻ በማውጣት ገንዘቡ እንደሚያደርገው፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔርን ድምጽ ከመስማት ርቆ በመሄድ የበደለውን የእኛን ማንነት ራሱ አምኖ ስለእኛ ኃጢአት የሌለበትን ኃጢአተኛ በማድረግ (2ቆሮ. 5፥21) ስለ እኛ መርገም ሆኖልን (ገላ. 3፥13) ተቀጥቶ፤ ክሶ፤ ተቤዥቶ ነጻ በማውጣት ያለክርስቶስ የነበርነው በክርስቶስ ለክርስቶስ አደረገን። ከሕግ  እርግማንም ዋጀን።

ይቀጥላል…

3 comments:

  1. amen amen amen

    ReplyDelete
  2. May the grace of God and the SPIRIT be your strength. GOD bless you for sharing.

    ReplyDelete
  3. I love the way your teaching

    ReplyDelete