ካለፈው የቀጠለ…
ይህን ማወቅ ለምን አስፈለገ?
እግዚአብሔር ሃይማኖታዊ ዝንባሌና መልኩ ብቻ እንዲኖረን አይወድም። “ሙሉ ሰው ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ” ለማደግ፥ “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት መምጣት (ኤፌ. 4፥13)፤ ስለ እውነት ስለ እግዚአብሔር ልጅ ዕውቀት ሊኖረን ይገባል።
ስለ እውነትና ስለ እግዚአብሔር ልጅ ለማወቅ ሁለት መሠረታዊ
ነገሮች ተጠቅሰዋል። አንድነትና ማደግ።
አንድነት፦ ክርስቶስን በማመን ከመንፈስ ቅዱስ የሆነ አንድነትን ያሳያል።
“እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ
ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን
አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት
አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።” (ኤፌ.4፥1-6) |
ይህም ያመኑትን አመኞች የሚያመለከት ነው። ቤተ
ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት። እርሱ ደግሞ ራሷ። በቤተ ክርስቲያን ላይ ዋና ብቸኛ ሥልጣን ያለው ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው።
የቤተ ክርስቲያን አንድነት የተገኘው ጌታ አብ በልጁ ክርስቶስ እንዳይበላሽ ከባድ ኃላፊነት አለባቸው። ክርስቲያኖች ሁሉ ይህ አንድነት
ቤተ ክርስቲያን ይህን አንድነት “በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ” (ሐዋ. 2፥42) እንደ ነበረው፥
ክርስቲያኖች የክርስቶስ ሞቱን፣ መቀበሩንና ትንሣኤውን፥ በዚህም የተገኘውን የኃጢአት ሥርየትና መዳንን የሚያውጀውን ጌታ ያስተማረውን
የሐዋርያትን ትምህርት በማጽናት አንድ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
አንድነት የበጉ መንግሥት ዋና መገለጫ ነው፤ (ራእ.
20፥4) በዚህች ምድር ያለችም ቤተ ክርስቲያን [ክርስቲያኖች] አንድነት ዋና ነገሯ መሆኗን መዘንጋት የለባትም። በአንድነቱ ውስጥ የሚሰጡት ልዩ ልዩ ጸጋዎችም “የክርስቶስ አካል ይገነባ ዘንድ” (ኤፌ. 4፥12 ዓ.መ.ት) ነው እንጂ
ለግል ጥቅም ወይም በአንድነቱ ውስጥ ምዕመናን ሥራቸውን ራሳቸው እንዲሠሩ የሚያዘጋጇቸው ናቸው። ቤተ ክርስቲያን እንድናገለግልበት
የተሰጠንን ጸጋ ለግል ጥቅም ማዋል አስነዋሪ ኃጢአት ሰው፤ ሰጪው በመጣ ጊዜ በፍርድ ይቀበለናል።
ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ያንን ሁሉ
መከራ ከፍሏል። የግል ሕይወትን አብልጠን ለረተረገነባ ያለችን የክርስቶስ አንድነትና የቤተ ክርስቲያን አካል ቸል ብንል ተግሳጹ
ያገኘናል።
ማደግ፦ የምናድገው “በክርስቶስ ወዳላው
ፍጹምነት” ነው። ስናድግም ከአንድነቱ ሳንነጠል በዚያው ውስጥ እያለን ነው። በግል የምናድገው የራሳችን ዕድገት የለንም። የተሰጠንን መንፈሳዊ ጸጋ ሙሉ ለሙሉ ለቤተ ክርስቲያን
እንጂ ለራሳችን ማዋል እንደሌለብን አንስተናል። አካሉ ወደፍጹም ሙላት፤ ሕንጻው ወደፍጹምነት እንዲያድግ ከተፈለገ እያንዳንዱ ብልት
ወይም የሕንጻው ክፍል ራሱን እንዲችል መሥራት ይገባል።
አገልጋዮች ምዕናንንን ወደ ክርስቶስ መሳብና ማሳደግ
አለባቸው እንጂ ሁል ጊዜ በሞግዚትነት ሊመሯቸውና ሊጠብቋቸው ይገባል። የተጠናቀቀ ሕንጻ አገልግሎ ራሱን ችሎ እንደሚሰጥ፣ ሁሌም
ሲታነጽ እንደማይኖር ሁሉ፣ ሁል ጊዜ እየተሠራን በሚያኖር ማንነት
መኖር የለብንም። ሁሉ ጊዜ ቃሉን የምናስጠናቸው፤ መልሶቻቸውን የምንመልስላቸው፤ ያለእኛ ሙሉ እንዳልሆኑ እንዲያስቡ ከማድረግ ልንከለክል
ይገባል።
በራሳቸው የሐሰትና የእውነት መምህራንን ትምህርት
መመርመር የሚችሉበትን ጥበብ ልናሳያቸው፤ ወደቤርያዊ ልበ ሰፊነት(ሐዋ. 18፥10) እንዲደርሱ መንገድን ማሳየት አለብን። የሰውነታችን
አካላት ሁሉም እኩል እንዲያድጉ፤ አንዱ ግን አስተዳደጉ ቢያስተጓጉል፣ ብዙ ነገር እንደሚያስተጓጉለው የክርስቶስ አካላት የሆኑትም
ምዕመናንም ሁሉ ከጸጋ ሳይጐድሉ ፍጹም በእኩልነት ሊያድጉ የሚችሉባቸውን መልካምና የተመሰከረለትን ሥራ ልንሠራ ይገባናል።
በክርስትና ትምህርት ዕውቀት ወይም ከሌሎች ሰዎች
ጋር ባለን ግንኙነት የሚገልጠውን የግል ብስለት ሳይሆን ፍጹም ሚዛናዊ በሆነው በክርስቶስ ባሕርይን ማደግን ያሳያል። ይህም በዓላማ
አንድ መሆንንም ጭምር የሚያሳይ ነው። ጌታ ኢየሱስ የሁሉንም አካላቱን ጤንነቱን እጅግ ይፈልጋቸዋል። የእኛ ብርታት ብቻውን አይቆምም፤
ዓይን ጤናማ ቢሆንም ደኅንነቱ በሌሎች ብልቶች ላይ ይመሠረታል። የአንዱ ክርስቲያን ሕብረት ድካምና ውድቀትም የሌላውን ክርስቲያን
ሕብረት ማስነቀፉና ማዋረዱ አይቀርም። ስለዚህም ወደ ክርስቶስ ስናድግ የተከፈለልንን እናስተውል፥ እርሱን “የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን
በመመልከት” (ዕብ. 3፥1) ሕንጻው እየተጋጠመ ውብ ቤት እንደሚሆንና እንደሚሠራ ሁላችን ለክርስቶስ ቤትነት የተገባን ቤት
ሆነን እንሠራ ዘንድ ወደ ክርስቶስ ተያይዘን ልናድግ፤ ልንተናነጽ ይገባናል።
በረድኤተ ኢየሱስ ተፈጸመ!
11/6/2005 ተጽፎ ጥቂት ተሻሽሎ ቀረበ!
God bless you this is my message
ReplyDeleteBless you more!
ReplyDelete