Tuesday 20 October 2020

ስላንተ ልጣላት

Please read in PDF

አልወድህም አንተን አልወድህም የምር
ከአንደበት አያልፍም ላንተ ያለኝ ፍቅር

የተገበዘ ነው ነገረ ሥራዬ
እኔ ነኝ ማእከሉ ለእኔ ነው ሩጫዬ።


አየህ አማኑኤል፣  ከኔ ጋር ያለኸው?
ደስታዬ እኔ ነኝ ክብሬን ነው ማገነው።
እናም እባክህን ዓይኔን ከእኔ አንሣ
ስላንተ ልጣላት ነፍሴንም ሳልሳሳ።
በመጨረሻው ቀን አንገት እንዳልደፋ
መውደድህን ስጠኝ ትእዛዝህንም ልፍራ።

1 comment:

  1. የሰላምና የበረከት አባት ያብዛh

    ReplyDelete