Sunday 7 June 2020

ጰራቅሊጦስ

Please read in PDF
በምድር ዳርቻ ፍጹም ምድረ በዳ
ደግሞ በእልፍኜ በውስጤ ውስጥ ጓዲያ
በመከራ ሰዓት በመከሩ ደስታ

በማጣት በማግኘት ኹሌ የማትጠፋ
አንተ ነህ አጽናኙ አብረኸን የምትኖር
በፍቅር እየታዘብክ አንዴም ሳትቀየር።
ደካማ እንደʼንቦሳ ʼምታዘልል ብርቱ
በጨለማ ላለ ማለዳ ንጋቱ
የራቀ ʼምታቀርብ የረቀቀ አጉዪ
ጰራቅሊጦስ አንተ ፍጹም መስተፈስሒ …
አንተ ነህ ቅዱሱ ጰራቅሊጦሳችን
በመስቀል ቸንክረህ ያኖርከን ጸጋችን!!!
ለስዱዳን ታዛ ለሰማዕታት ደስታ
የሰባኪያን ፋኖስ የዘማሪያን ʼልልታ
የሐዋርያት ሥልጣን “የበተስኪያን” ማጫ
ኹሌ የምትመግብ የሕይወት ቃል ብቻ
አንተ ነህ አጽናኙ መሪ መምህራችን
የዓውደ ምሕረት ብርሃን ፍኖተ ካርታችን!

1 comment: