Wednesday 24 June 2020

ድንገት እንዳይደፋን!

Please read in PDF

ትንሺቱ አዚም እጀ ሰብዕ ጥንቆላ
እንዴት ቀዬአችንን፤ እርሻችንን ትብላ?

ቅንአታችን ሳይቀር እንደ ምን ይከላ? …
ምነው ምን አገኘው ትውልድ የታለለ
ተንፏቆ ተንፏቆ እንደ ሕፃን የዳኸ?!
አዚም ከየት መጣ ጽኑ ድንዛዜ
ሃይ ሎጋነት በዛ የኑፋቄ ሚዜ።
እንዲህ ይኾን እንዴ? …
መጽሐፉ ተረሳ መሲህ ተዘነጋ
እኔነት በአትሮንሱ እንደ ቆመ ነጋ።
እንዲህ ይኾን እንዴ? …
እምነት በኹኔታ ተፈረካከሰ
ከመለኮት ይልቅ ሰውነት ነገሠ…
እንዲህ ይኾን እንዴ? …
አቤቱ መልሰን እንመለሳለን
ከወደድነው ጌታ ከአዚም አስጥለን
እንደገና ሥራን እንደገና ጌታ
ድንገት እንዳይደፋን የአዚም ትንታ!!!


2 comments: