Friday 30 November 2018

በደጅ ነው!

Please read in PDF

እዚያ ማዶ ጭስ ይጨሳል
ከዚህ ማዶ ፍህም አመድ ይወልዳል
እዚያ ማዶ ይበርዳሉ
እዚህ ማዶ ለብበዋል [ለብ ብለዋል]

እዚያ ማዶ ሥጋ ለባሽ ያገናሉ
እዚህ ማዶ ጮማ ግብር በሙት መንፈስ፣ አመካኝተው ይበላሉ
እዚያ ማዶ የእውነት ምሷ ተደርምሶ፣ ልትቀበር ጥቂት ቀርቷል

እኮ ወዴት ውጦ ውጦ
ዐመጻውን ስለቃቅጦ?
ምነው ባየሽ ዘመንሽን
መቀዳዱ ቀሚስሽን
“ለምን ብቻ ያ አርዮስ” ይወገዛል?
አንቺም እኮ ከደባትራን ፓስተሮችሽ ተደርተሻል
ቤተ-ኢየሱስ መኾንሽን በእኩይ - ግብርሽ ተቃውመሻል
ቤተ-እምነት ቤተ- ክርስቲያን መራቆትሽን አይተሽዋል?

በጭላንጭል የዕድሜ ዕላቂ
አክባሪሽን ባታከብሪ
ሞገስሽን ባትፈሪ
በፊቱ ንስሐ በቶሎ ባትገቢ
በደጅ ነው የፍርዱ ቃል ከፈጣሪ!!!
እግዚኦ መሐረነ
    ››  መሐከነ
    ››  ተሣሐለነ!!!

(21/3/2007 ሐረር ከተማ ከመኪና አደጋ በተረፍኩ በማግስቱ ተጻፈ፡፡)

1 comment:

  1. bataskann kemesadeb mech new mtarfew ante lj?

    ReplyDelete