Thursday 29 June 2017

“እኔ” ሥልጣን ይጣ!

አርነት አታውጣኝ ለሥጋ ፈቃዴ፣
ነጻነት አትስጠኝ እንድሆን መደዴ፤
የቃልህን ብርሃን በዝቶልኝ ካየሁህ፣

አይቼህ ቀምሼህ አንተን ካጣጣምኩህ፣
ድምጽህን ቃልህን ብዙ ከለመድኩህ፤ …
ደግሞም ብዙ ሕይወት ካተረፍኩ በኋላ፣
ዳግመኛ እንዳልያዝ በዚህ ዓለም ተድላ፡፡

አትስጠኝ ለራሴ ለገዛ ምኞቴ፣
በፍቅር ጠቅጥቀህ ያዘኝ ውድ አባቴ!
ይቅርብኝ ለኃጢአት ይቅርብኝ ነጻነት፣
ከዳኑ በኋላ ርኩሰትን መመኘት!
ጤናውም ይቅርብኝ ገንዘቡም ለምኔ፣
ካልሾምኩህ ንጉሤን ካልነገሥክ በእኔ፣
ምንድንስ ይባላል የምቆጥረው ዕድሜ!?
ጌታዬ ኢየሱስ!
አቤቱ ክርስቶስ!
ባንተ ስም ከኃጢአት አርነት ስወጣ

ንገሥ በፈቃዴም “እኔ” ሥልጣን ይጣ!!! አሜን፡፡

No comments:

Post a Comment