Wednesday 14 June 2017

አታወሳስቡብን!

ውስብስብ አይደለም ያልተብራራ ቅኔ
ለእርሱ እንደተገባሁ ኃጢአተኛው እኔ፤
ለብዙ ኃጢአቴ እልፍ ምሕረት ፈሶ

ድኜ ቀርቻለሁ ውስጤ ተቀድሶ፤
ጌታችን ኢየሱስ የዓለም መድኃኒት
ግልጥ ነው ቤዝወቱ ዛሬም ለታመኑት፤
አታወሳስቡብን መቅረቢያ መንገዱን
ካጐበጠን ሸክም በእርሱ አምነን እንዳን፡፡


No comments:

Post a Comment