Wednesday 4 March 2015

ይገባሃል

ይገባሃል!


                               Please read in PDF



“ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋን ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሕይወት ለሚኖረው እየሰገዱ። ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና ስለ ፈቃድህም ሆነዋልና ተፈጥረውማልና ክብር ውዳሴ ኃይልም ልትቀበል ይገባሃል እያሉ በዙፋኑ ፊት አክሊላቸውን ያኖራሉ።”
(ራዕ.4፥10-11)



ይገባሃል ውዳሴ
ይገባሃል ቅዳሴ
ይገባሃል ዕልልታ
ይገባሃል ማኅተሙንም ልትፈታ
ይገባሃል የማያቋርጥ ግርግርታ፡፡

 ይገባሃል መወድስ
ይገባሃል መባል ቅዱስ
ይገባሃል መባረክ
ይገባሃል ከፍ ከፍ ማለት
ይገባሃል ክብርና ምስጋና፡፡
ይገባሃል አዲስ ቅኔ
ይገባሃል በማይደክም ልሳን ዝማሬ፡፡
ይገባሃል ኃይልና ጥበብ
ይገባሃል አንክሮ
ይገባሃል ተዘክሮ
ይገባሃል ሆታ
ይገባሃል የዘንባባ ዝንጣፊ
ይገባሃል ጌትነት
ይገባሃል አሜናችን
ስላዳንከን ክበርልን ረድኤታችን፡፡


ንጉሣችን ክርስቶስ ሆይ! ክብር ሁሉ ተጠቅልሎ ለአንተና ለመንግሥትህ ብቻ ይሁን፡፡ አሜን፡፡

1 comment: