Thursday 19 March 2015

እኔ ላንተ ፈራሁ!


                                  Please read in PDF 


ትመስለኝ ነበረ፣ ለጨለማው ብርሃን ፣ ለጣዕም አልባው ጨው
ትመስለኝ ነበረ፣ ለብ ያለውን ሁሉ ፣ ግለህ ʻምታግለው
ትመስለኝ ነበረ፣ ብርሃንህ የበራ ከእንቅብ በላይ ሆኖ
ትመስለኝ ነበረ፣ ከጨለማ በላይ ከጋኑም ከፍ ብሎ

ትመስለኝ ነበረ፣ እንደአገልግሎትህ ጆሮህም የቀና
ትመስለኝ ነበረ፣ ለክፉ ደንቁረህ መልካም የምትሠማ፡፡
ዳሩ …
አይደለህም አንተ ለእውነት የምትወግን
ከጌታ ጋር ቆመህ ለጌታ ʻምትጨክን
ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ስትልማ ላየህ
           የአምልኮ መልክ አለህ
በብዙ የቃል ጥበብ ምስጢር ታወራለህ፡፡

ሲመጣ ግን ጌታ ከለምለሙ ዛፍ ላይ ፍሬውን ፍለጋ
እኔ ላ'ንተ ፈራሁ ተቆርጠህ ከእርሱ ከግንዱ ስትወጣ፡፡


No comments:

Post a Comment