Tuesday 10 March 2015

ሰው የለንም ጌታ!


                Please read in PDF

አንቀልባው አረጀ ደከመ አልጋችን
ፈውስህ ራቀንና ቃሬዛ በዛብን
ጎብጦ ሳይል ቀና ኑሮ እንዳከሰለው
ቀኑ እንደጨለመ ይሄዳል ሰው ይኸው፡፡ 

ኃጢአት አለመጸን መሳለቂያ ሆንን
የሞትክልን ፍቅር አንተን አሰደብን፡፡
አቤቱ አስነሳ ደግ ሰው  ይነሳ
ሰው የለም ባ'ገሩ ላ'ንተ የተገዛ
ቆሞ 'ሚሄደውም ባይዝ እንጂ አልጋ
ታሞ ያቃስታል በነፍስ በሥጋ
ልክ እንደመጻጉዕ ባናውቅህም ጌታ

ሰው የለንም ማረን እስራችንን ፍታ፡፡ 

No comments:

Post a Comment