Thursday 7 November 2013

የቆምኩኝ ሲመስለኝ



ማዘያው ከጠፋ የህፃን አንቀልባ
መልካሙ ተጣሞ ካጨድን ገለባ
አፅናኙ ተክዞ መፅናናትን ካጣ
የቆመ የሚመስለው ጎብጦብን ከመጣ
ረሀብ አጠውልጎት  ህፃን ካለቀሰ
ጻድቅ መላ ጠፍቶት ሰይጣን ከቀየሰ


ብርታት አጎንብሶ ድካም ፀንቶ እግሩ
ይሁዳና ዴማስ ጽድቅ ከመከሩ
ሳዖልና ኬፋ ደግ ካልተስማሙ
አቤቱ ለባሪያህ መንገዱን አብራለት
ማየትና መስማት ካንተ ይሁንለት።

ፈትልን የሚፈትል ተራቁቶ ካደረ
ውለታ የበዛለት በሳቅ ካልዘመረ
በብዙ የተሾመ ጥቂት ካልታመነ
ልብን አሳራፊው ልቡ ከጨከነ
ሰባኪ እየካደ ዓለሙ ካመነ

አማኙ ሲታበይ ቀራጭ አጐንብሶ
የጽድቁን አዝመራ ከወሰደ አፍሶ
አቤቱ ለባሪያህ አይነ ልቡን አብራ
የቆምኩኝ ሲመስለኝ እንዳልወድቅ አደራ።

ሥራዬ የሞት ነው ጽድቄ የመርገም ጨርቅ
አቤቱ አድነኝ በድካሜ ሳትፈርድ
ብርታትህ ያቁመኝ አንተን እንድመስል
ማስተዋሌን አድስ ያለማመኔን ቃል፡፡

3 comments:

  1. አቤኔዘር በርታ የረዳህ ጌታ ይባረክ
    አሸናፊ

    ReplyDelete
  2. Awesome bra thanks,one day I goon
    meet you,PS stay strong,u &ashu days come to u guys,I am really blessed on your scripture.God bless you.

    ReplyDelete
  3. አቤቱ ለባሪያህ መንገዱን አብራለት
    ማየት እና መስማት ካንተ ይሁንለት።betam des ylal Egziabher ybarkih berta!!!

    ReplyDelete