Friday 22 November 2013

የእግዚአብሔር ትራፊ

ከግምት ከበዛው ከማይቆጠረው
ከተትረፈረፈው ጨብጠን ከያዝነው
ከአምስቱ አሳና ከሁለቱ እንጀራ
አለን ከምንለው ከኛ ብዙ ዝና
ይደንቀኛል ይገርመኛል የአምላኬ ሥራ!!


አዕላፍ መግቦ በብዙ በረከት
በፀጋው ተረፈ አስራ ሁለት ቅርጫት
የእግዚአብሔር  ትራፊ እኛ ካለን በልጧል
ዕልልታ ለስሙ ምስጋናውም በዝቷል
ይልቅ አትመኩ አለን እያላችሁ
ከታላቁ ጌታ እግሩ ስር ወድቃችሁ
የጽድቅ ፍርፋሪ ለምኑ ባካችሁ

ከከነናዊቷ ሕይወት ተምራችሁ፡፡

No comments:

Post a Comment