Tuesday 19 November 2013

ነፍሴ አንተን ብቻ



ወንድሜን አሳዳጅ ቃየላዊ እብደቴ፣
ጥርጥር የሚነዳው ዲዲሞስነቴ፣
ኬፋዊ ግርግር ችኩል የሚያሮጠው
ሄሮድሳዊ መርገም የህፃን ደም 'ሚጥመው፣



ሳኦላዊ ስሜት ቀለብላባነቴ
አጋርን 'ሚገፋ ሳራ ሰውነቴ፣
ያዕቆብን 'ሚጠላ ኤዶማዊነቴ፣
ማስታረቅ የማይችል ርብቃ ማህጸኔን፣
አለምን ናፋቂ ዴማሳዊ ህይወቴን፣
ከጠወለገ ገጽ የኤማሁስ ተጓዥ፣
ለሀገር ከማይረባ ከኤካቦድ አርጋዥ፣
አልጋ ሲሉት ቀጋ ከይሁዳዊ ሩጫ፣
እረፍት ከጠፋበት ከሌለው ማምለጫ፣
ጠብቀው ባርያህን ስራኝ ላንተ ፈቃድ፣
ነፍሴ አንተን ብቻ ለዘላለም ትውደድ።

No comments:

Post a Comment