Wednesday, 20 September 2023

ነገረ ሥላሴን የምናጠናበት ምክንያት (ክፍል ፪)

 Please read in PDF

ካለፈው የቀጠለ …

2.4. እውነትን በመኖር ለማደግ

እውነተኛ ዕውቀት አእምሮን ጤናማ ያደርጋል። እውነተኛ ዕውቀትና ጤናማ ትምህርት የሌላቸው ሕይወታቸውና ልምዳቸውም ጤናማ ሊኾን አይችልም። በክርስትና ትምህርት ስናውቅ እናምናለን፤ ስናምነው ደግሞ የምናውቀው ብዙ አለን። የእምነት ዕድገት የሕይወት፣ የአምልኮና የመንፈሳዊ ዕድገት ለውጥ ነው።

ቅዱስ ጳውሎስ፣ “የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።” (ኤፌ. 1፥17) በማለት፣ እግዚአብሔርን በማወቅ እንዲያድጉ የጥበብና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣቸው ልመና ያቀርባል። ይህም ዕውቀት ከራሱ ከእግዚአብሔር እንጂ ከሌላ ከማንም ሊመጣ እንደማይችልም ጭምር ይናገራል።

በሌላ ስፍራም፣ “ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።” (ኤፌ. 4፥12-13) እንዲል የጸጋ ስጦታዎች ኹሉ የሚሰጡትና የሚታደሉት ወደ ክርስቶስ ሙላቱ ልክ እንድናድግ ነው።

ከዚህም የተነሣ፣ አውቀነው በፍጹም ያልታዘዝነው ደግሞም ያልኖርነው እውነት፣ ከሐሰተኝነት በምንም አይተናነስም፤ በጌታ ትምህርት የፈሪሳዊነት አንዱ መገለጫም፣ ላመኑት እውነት ፍጹም አለመታዘዝ ነው።

      3. የምናጠናበትን ወይም የምንማርበትን ዓላማዎች የሚያጸኑ ምክንያቶች፦

3.1. ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው።

ትምህርተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ነው። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ኹሉ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊ ነው። ኦርቶዶክሳዊነት ምንድር ነው?

ኦርቶዶክስ ማለት ኦርቶ ርቱዕ፤ ዶክስ ባህል ሐሳብ፣ ኅሊና፣ ስብሐት፣ ምስጋና ይኾናል፤ በተገናኝ ርቱዐ ሃይማኖት ማለት ነው። … ኦርቶዶክሳዊ ማለት ደግሞ የኦርቶዶክሳዊ ወገን እውነተኛ ቅን፣ በሃይማኖቱ ሐሰትና ስህተት ጽነት የሌለበት።[1]

ከዚህ የምንረዳው ኦርቶዶክሳዊነት ጥንተ ስያሜው ትምህርትን እንጂ፣ ተቋምን ወይም የአንድ ቡድን መጠሪያ የሚያመለክት አይደለም። ትምህርትን ያመለክታል ስንልም፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሐሰትና ስህተት ጽነት የሌለበትን ማለታችን ነው። እንግዲህ ትምህርተ ሥላሴ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተቀዳ እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ነው። እንግዲህ እንዲህ ማለት እንችላለን፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኹሉ ኦርቶዶክሳዊ ሲኾን፣ ዛሬ ላይ የምናየው ኦርቶዶክሳዊ ኹሉ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው ማለት አንችልም።

ትምህርተ ሥላሴ መጽሐፍ ቅዱስ ባልተጻፈበትም ዘመን የታመነ እውነት ነው። ስለዚህም ባይገባንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱሳዊ በመኾኑ ብቻ ልንታመነውና ልንኖርበት ይገባናል። ምክንያቱም እምነታችን የሚጀምረው ይህን ከማመን ነውና። መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነትና እውነት ደግሞ ፈጽሞ ቸል ሊባል አይገባም።

3.2. አምልኮአችን ሥላሴን በመረዳት ላይ የተመሠረተ ነው፤

አምልኮአችን የሥላሴ ስምን በመጥራትና በመደጋገም፣ ከታላቅ አክብሮትም የተነሣ ስሙን በመፍራት ማዕከል ያደረገ ነው። የእግዚአብሔር ስም ይባርካል (ዘዳ. 21፥5፤ 1ዜና. 23፥13)፣ የእግዚአብሔር ስም በአምልኮ ይታወጃል (ዘጸ. 34፥5)፣ የሚያመልኩት ኹሉ የእግዚአብሔርን ስም ሊያጐሳቍሉ አይገባቸውም (ዘሌ. 21፥6)፣ “«አምላክህ እግዚአብሔር» የተባለውን የተመሰገነውንና የተፈራውን ስም ባትፈራ፥ …” (ዘዳ. 28፥58፤ መዝ. 29፥2) ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ አማኞች ኹሉ ይህን ስም ሊፈሩትና እጅግ በአምልኮ ዘወትር ሊያከብሩት (መዝ. 66፥2፤ 96፥8)፣ በስሙ ልንጓደድ (ኰራ፤ ኰራ ልንል) (1ዜና. 16፥10፤ መዝ. 105፥3) ይገባናል።

ምክንያቱም ስሙ፣ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ ይመሰክሩለታል” (ሐ.ሥ. 10፥43) እንዲል የኀጢአትን ሥርየት ይሰጣል (ሉቃ. 24፥47፤ 1ዮሐ. 2፥12)፣ ስሙ የጸና ግንብ ነው (ምሳ. 18፥10)፣ ስሙ ሕይወታችን ነው (ዮሐ. 20፥31)፣ ስሙ ይታመናል (ዮሐ. 3፥18፤ ሐ.ሥ. 3፥16፤ 10፥43፤ ሮሜ 1፥5)።

እግዚአብሔርና ስሙ አንድ ናቸው፤ ሰለሞን መቅደሱን ለእግዚአብሔር በሠራ ጊዜ ምን እንደ ተናገረ እናስተውል፣ “… ለእስራኤልም አምላክ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ።” (1ነገ. 8፥20) እንዲል፣ እግዚአብሔርና ስሙ ሊነጣጠሉ አይችሉም። ቅዳሴአችን “አብ ቅዱስ ነው፤ ወልድ ቅዱስ ነው መንፈስ ቅዱስም ቅዱስ ነው” ብሎ፣ ሲዘጋም ወይም ሲጨርስም፣ “ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ” የሚል ነው።

ስለዚህም ሥላሴንና ስሙን ከአምልኮ መንቀል ወይም መነጠል፣ መንፈሳዊ ኹለንተናን ያነቅዛል። ድነናል ካልን፣ በዚህ ስም መታመን፣ በሥላሴ ውስጥ መግባትና መኖር፣ እርሱን በማምለክ ብቻም ልን ጸና ይገባናል።

ይቀጥላል …



[1] ኪዳነ ወልድ ክፍሌ(አለቃ)፤ ገጽ 243

5 comments:

  1. ABE, WOLDE,MENFES KIDUSE .THIS IS TRINITY AND YOU CAN FIND IT ALLOVER IN THE BIBLE IF YOU WANT.

    ReplyDelete
  2. My brother, for you it is very mysterious to know about the mystery of the Holy Trinity. If you really want to know about it you have to ask to the giver of wisdom and knowledge which is the Holy Spirit. And also you have to study the holy bible from the true scholars of the bible. There is no mistaken, saying that, God is one in three and three in one. He is three in name, three in person and three in deed, but when we say they are three in names. . We are not saying there are three gods but One True God. God the Father, God the Son and God the Holy Spirit One true God. We are all baptized in the name of the Father, of the Son and of the Holy Spirit one God. please read Matthew chapter 28:19-20 with understanding and please pray before starting reading it. may the Holy Spirit opens the ear of you heart.

    ReplyDelete
  3. Okay. That verse is primarily for Jesus Christ of course, but it can be for St. Mary secondarily. Don't over stretch facts. I think Aba Heriakos also calls St. Mary as the "Ladder of Jacob." All is secondary... What is wrong for the Mother to be called with some of the qualities of Her most beloved Son, who is the fruit of Her Womb? Again, it is not that helpful to fight on this. Better to focus on other areas of improvement. Let's get the debteras and some other followers out of tinkola and other bad beliefs. The mainly Pente West has approved gays and lesbians to be bishops of the church of Christ; it may not be long before we see similar demands by ethiopian pentes. At least, no orthodox is accused of that... Better fight the evil; St. Mary is the Mother of Christ and has no parllel for Her. Even if your verse applies solely for Jesus Christ, it won't affect Her and nor our love for Her. Again, it is better to focus on other value-adding areas if you are a genuine christian.

    ReplyDelete
  4. እየቀለድህ ነው አይደል? What do you mean by primary and secondary? Come on! let's stop confusing ourselves and others. A given word of God in the Bible has one and only one message for all of us. Primary, Secondary የሚለው ዝባዝንኬ ጸሐፊው እንዳለው የስህተት ትምህርቶችን እውቅና ለመስጠት የተደረገ ነው። እመቤታችንን ለማክበር የግድ ለክርስቶስ የተነገረውን ለእርሷ ማድረግ የለብንም።ይሄ የእግዚአብሔርን ቃል ማጣመም ነው። ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን ግን ያለቦታው እና የመጽሐፍን ትርጉም በማዛባት አይደለም። YOur argument regarding some protestant's views on gays and lesbians is confusing. Are you saying we should stop discussing all other issues because of this? I think the witter has a valid point and has done a good job of pointing out a dangerous trend in our church to use the Bible in the wrong way to justify or exagerate some things. I don't understand your view of "value adding areas" Should we just talk about Pentes, Gays, Lesbians? please make yourself clear. ለክርስቶስ የተነገረው ክብር, ማንነት ለሌላ መሰጠቱ፥ ላንተ ምንም ላይሆን ይችላል።ለአንዳንዶቻችን ደግሞ እጅግ ያሳዝናል። ጥያቄው እኮ እግዚአብሔር ለያዕቆብ ያንን ህልም ሲያሳየው ሊያስተላልፍ የውደደው መልዕክት ምንድን ነው? ነው። መልዕክቱ አንድ እና አንድ ነው። እንደዚህም ነው እንደዛም ነው የሚለው ማወናበድ ስህተት ነው!

    ReplyDelete
  5. God bless you. Its amazing and powerful article

    ReplyDelete