የሰቆቃ አድማስ ተንዶ ሲፈጨኝ
ዋይታና እሪታ ምግብ መጠጥ ሲኾነኝ
እንደ ዘጠኝ ወር ምጥ
በየቀኑ ሳምጥ
ሰቀቀን ወዳጄ ሐዘን ባልንጀራ
ደስታና ፈገግታ ከእኔ ተቀያይመው ኾነው ባላጋራ
ሲያድሙ ከልቅሶ ከእንባዬ ጋራ
ባክህ ደስታዬ ሆይ ና ወደኔ ግባ!
ና ግባ ከቤቴ ኹሌ በየቀኑ
ስብራት ይወገድ ይነቀል ችንካሩ!
ይብገን ቅጥል ይበል የልቅሶ ሸለቆ
ሳቅህ በየቀኑ በቤቴ ላይ ደምቆ
የክብር ንጉሥ ሆይ! ወደ ቤቴ ግባ
ተመላለስበት ብቻህን አባባ
ብበድልህ እንኳ ገብተህ ባክህ አትውጣ
እንደገና ሠርተህ ክበርብኝ ጌታ!
No comments:
Post a Comment