Friday 14 April 2023

እናንተ ባሮች ሆይ...!

 Please read in PDF

ንጉሥ በባዶነት ዝቅ አለ ወረደ

አሮጌውን አዳም በአዲስ አስወገደ

ደግሞ...!

ንጉሡ ዝቅ ብሎ መታዘዝ "ተማረ"

ሕማም የማያውቀው፣ ሰውን ስለ ማዳን ሕማምን ታመመ!

ንጉሡ ውድ ነው ተወዳጅ ትምህርቱ

ንድፍ ብቻ ሳይኾን ይገዛል ሕይወቱ

ኩራት አስወግዱ ተዉ አትታበዩ

ጌታ የኾነውን ይህን ባሪያ እዩ!

ንጉሥና ባሪያ ባንድ ባይስማሙም

በኢየሱስ አይተናል አካል ነሥተው ፍጹም!

እንኪያስ

በየሜዳው መጮኽ ይቅር አትለፍፉ

እናንተ ባሮች ሆይ...!

ጌታን አክብሩና እናንተ እለፉ፣

አስከብሩትና እናንተ ተረሱ

ይህ ነው ዋና ትምህርት የኢየሱስ ንጉሡ!

No comments:

Post a Comment