Sunday 17 April 2022

የኛ ዘመን አማኝ!

 Please read in PDF

ገበታ ዘርግተው ርግብ ሚሸቅጡ

የመሥዋዕቱን ዋጋ በብር ሚለውጡ

ጨካኝ ነጋዴዎች የነፍስ ደላሎች

በከበቡ ጊዜ የኪስ ቦጥባጪዎች...

ጅራፍህን ገምደህ ገርፈህ ያስወጣኸው

ጻድቁ ጌታችን ሥራህ ትክክል ነው!

ዛሬም እንዳየኸው የትላንቱ ኾኖአል

ርግቡ፣ በውኃና ዘይት በሶፍት ተተክቷል

የበሬና የበግ ገበያው ተጧጡፏል...

ጅራፍ የሚያነሳው ፍቅር አልባ ተብሏል

በግና ተኩላ አውድድ ካውንስል ተሹሟል...

እናም ጌታችን ሆይ፤

ወደ ገዛ ቤትህ በተስኪያን ስትመጣ

ዘይትና ውኃ ጠጪ ስለ በዛ

ቢንቁ አትደነቅ የደምህን ዋጋ...

እኔን የጨነቀኝ

እኔን የሰቀቀኝ

ጅራፉ አርፎበት በሰንበር በልዞ

የኛ ዘመን አማኝ መች ያይና ነፍዞ!

1 comment:

  1. እኔ እንጃ ምን ማለት እንዳለብኝ እግዚአብሔር ይህን የምትሰራውን አይቶ ሀሳብህን ያሳካልህ።

    ReplyDelete