Sunday 17 April 2022

አቅናን እባክህን!

 Please read in PDF

ይገባሃል ክብር መባል ሆሳዕና

ከመስቀሉ ስትሸሽ አልታየኽምና

ሆሳዕና ላንተ ዝቅ ላልከው ጌታ

"ጌትነትን" ንቀህ ወደኛ ለመጣህ።

 

ጌታ ሆይ፣

ንግሥናን አፍቅረን መስቀሉን ለጠላን

"ሆሳዕና"ን ናፍቀን ነቀፋን ላልጠገብን

መድኀኒት ስምህን ሸሽገን ለቀበርን

መድኃኒት መሳዮች ኮተቶች ለሸከፍን...

ተፈትቶ ቤታችን ወና ሳይኾን ደርሰህ

አቅናን እባክህን ፈውሰን መልሰህ!

No comments:

Post a Comment