Monday 16 April 2018

“ዓለም ያለድንግል ማርያም አማላጅነት አይድንም” ማለት፥ የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ ማክፋፋት ነው! (የመጨረሻ ክፍል)

Please read in PDF

ዓለም የሚድነው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ካመነ ብቻ ነው!
     ደቀ መዛሙርት ቅዱሱን ጰራቅሊጦስን እንደተቀበሉ ወዲያው ያስተማሩት እንዲህ የሚል ነው፦ “የሕይወትንም ራስ ገደላችሁት፤ እርሱን ግን እግዚአብሔር ከሙታን አስነሣው፥ ለዚህም ነገር እኛ ምስክሮች ነን” (ሐዋ.3፥15)፤ በመቀጠልም በሁለተኛው ቀን ስብከታቸው እንደገና፥ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” (ሐዋ.4፥12) ብለዋል፡፡ እውነት ነው እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ፦ “ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል”፤ (ሉቃ.24፥46-47)፡፡

     ደቀ መዛሙርቱ በስሙ የሆነውን ንስሐና የኃጢአትን ሥርየት እንጂ ሌላ አንዳች አልሰብኩም፤ መዳን ነው ብለውም አላወጁም፤ ስለመዳን የመሰከሩትና ያወጁት ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ በስሙ ንስሐንና የኃጢአትን ሥርየት ብቻ ነው፤ (ሐዋ.2፥36፤ 3፥15፡ 21-26፤ 4፥11፤ 5፥31፤ 6፥42፤ 7፥52፤ 8፥5፡ 35-40፤ 9፥20፤ 10፥34-43፡ 48፤ 11፥26፤ 12፥24፤ 13፥5፡ 12፡ 13-18፤ 14፥3፡ 7፡ 22፡ 27፤ 15፥35፤ 16፥13፡ 18፡ 31፤ 17፥3፤ 13፡ 18፤ 18፥25፤ 19፥5፡ 8፡ 20፤ 20፥28፤ 22፥8፤ 24፥8፡ 14፤ 26፥15፤ 28፥31) በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ብቻ ይህን የሚያህል ምስክር አለ)፡፡
     ከዚህ የተነሳ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የድኅነታችን መሠረትና የመዳናችን ዋና ነው፡፡ በእምነት የተቀበልነው ትልቁ የሕይወት ራስ እርሱ ብቻ ነው፡፡ በሥጋ የወለደችው የኢየሱስ እናት እንዲህ አለች፥ “መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች” (ሉቃ.1፥47)፡፡ አዎን! መድኃኒቷ መድኃኒታችን፤ አምላኳም አምላካችን ነው፡፡ በእርሱ በጌታችን ኢየሱስ እንጂ  በሌላ በማንም አልዳንንም፤ አንድንንም፡፡ ይልቁኑ ያለእርሱ ሌላ ወደአብ የምንገባበት በር የለንም፡፡ ቅዱሳን አባቶች ጌታ ክርስቶስን እንዲህ እንዳሉ፦ “ወደአባቱ ለመድረስ ጐዳና፤ ወደወለደው ለመግባት የሚሆን በር”፡፡
    እንኪያስ፦
ü  ው በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በማመኑ ከምን ዳነ?
-       ከኃጢአት (ዮሐ.1፥29 ፤ ሮሜ.3፥25 ፤ 5፥8 ፡ 1ዮሐ.2፥2 ፤ 4፥10)፤
-       ክፉ ከሆነው ከአሁኑ አለም (ገላ.1፥4)፤
-       ከዘላለም ፍርድ (ዮሐ.3፥17 ፤ 12፥48)
-       ከዘላለም ሞት (ዮሐ.3፥15 ፡ 36) በክርስቶስ ኢየሱስ ዳነ፡፡
    አሁን ደግሞ በመስቀሉ፣ በሞቱ፣ በደሙ ያገኘናቸውን ከድነታችን ጋር የተገናኙ ክንውኖች ከመጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝር እንመልከት።[1]

·         ከእግዚአብሔር ጋር የታረቅነው
ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን …” (ሮሜ 510)
ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋራ ያስታርቅ ዘንድ ነው። (ኤፌ. 216)
በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። (ቈላ. 119-20)
ልጁ በሥጋ በመሞቱ ምክንያት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ። (ቈላ. 122 1997 ትርጕም)

·         የኀጢአት ስርየትና ይቅርታ የተገኘው
ነፍሱን ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል (ኢሳ. 5310)

ስለ ብዙዎች ለኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው። (ማቴ. 2628)

እርሱንም [ኢየሱስ ክርስቶስንም] እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ አቆመው(ሮሜ 325)

መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ …” (1ቆሮ. 153)

በውድ ልጁም እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን በደሙ የተረገ ቤዛነታችንን አገኘን፤ እርሱም የበደላችን ስርየት።(ኤፌ. 17)

ክርስቶስ ደግሞ፣ የብዙዎችን ኀጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሠዋ በኋላ …” (ዕብ. 928)

በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነው ጌታችንን ኢየሱስን …” (ዕብ. 1320)

ለወደደን ከኀጢአታችንም በደሙ ላጠበን …” (ራእይ 16)

·         የእግዚአብሔር ፍቅርና ጸጋ የተገለጠው
ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። (ሮሜ 58)
ነፍሱን ስለ ወዳኞቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። (ዮሐ. 1513)

·         የጸደቅነው
ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቊጣው እንድናለን። (ሮሜ 59)
ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት ላይ ተሸከመ (1ጴጥ. 224)

·         ቤዛነታችንን ያገኘነው
በውድ ልጁም እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን በደሙ የተረገ ቤዛነታችንን አገኘን (ኤፌ. 17)

·         በእኛ ላይ ያለውን የሕግ ዕዳ የተሰረዘው
ሲቃወመንና ሲጻረረን የነበረውን የዕዳ ጽሕፈት ከነሕግጋቱ በመደምሰሰ፣ በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው። (ቈላ. 214 ..)

·         ሰይጣናዊ ኀይላት የተሸነፉት
የአለቆችንና የባለ ሥልጣናትንም ማዕረግ በመግፈፍ በመስቀሉ ድል ነሥቶ በአደባባይ እያዞራቸው እንዲታዩ አደረገ። (ቈላ. 215 ..)
ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያቢሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው (ዕብ. 214)

·         ታዛዥነቱ ጽድቃችን የሆነው
ለሞትም፣ ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። (ፊልጵ. 28)

·         ከሕግ እርግማን የተዋጀነው
በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን (ገላ. 313)

·         ለጽድቅ መሠረት የሆኑትን ግርዛትና መሰል ሃይማኖታዊ ሥርዐቶች የተሻሩት
ወንድሞቼ ሆይ! እኔ እስካሁን የምሰብከው፣ ለመዳን መገረዝ ያስፈልጋል እያልኩ ቢሆን ኖሮ እስከ አሁን ለምን ያሳድዱኝ ነበር? እንዲህ ቢሆን ኖሮ የክርስቶስ መስቀል ለሰዎች እንቅፋት መሆኑ ይቀር ነበር። (ገላ. 511 1997 ትርጕም)

·         ፈውስ ያገኘነው
ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀበእርሱ ቊስል እኛ ተፈወስን። (ኢሳ. 535)

·         ንጹሕ ኅሊና ሊሰጠን
ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?” (ዕብ. 914)

·         የእግዚአብሔር እንድንሆን
በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ..” (የሐዋ. 2028)

·         ቅዱሳንና ፍጹማን ሊያደርገን
ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና ስለዚህ በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም (1ቆሮ. 57-8)

እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፣ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።(ቈላ. 121-22)

ስለዚህ፥ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ። (ዕብ. 1312)

·         ወደ እግዚአብሔር የቀረብነው
   አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል። (ኤፌ. 213)

   ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና (1ጴጥ. 318)

·         ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ድፍረት እንድናገኝ
   በመረቀልን በአዲስና ሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን …” (ዕብ. 1019)

·         ከወረስነው ከንቱነት ሊታደገን
 ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ። (1ጴጥ. 118-19)

·         ለክርስቶስ እንጂ ለራሳችን እንዳንኖር
   በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።(2ቆሮ. 515)

·         መስቀሉን የትምክህታችን ሁሉ መሠረት ለማድረግ
   ነገር ግን፥ ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክሕት ከእኔ ይራቅ። (ገላ. 614)

·         ምሳሌውን እንድንከተል
    በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋራ መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን፥ የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። (ፊልጵ. 25-8)

የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፣ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስለ አለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። (ዕብ. 122)

·         የተበተኑትን በጎቹን ለመሰብሰብ
  ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው።ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን፥ የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ። (ዮሐ. 1150-52)

·         በዘሮች መካከል ያለውን ጠላትነት ለማስወገድ
    እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በዐዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን ዐዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን ባንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋራ ያስታርቅ ዘንድ ነው።(ኤፌ. 214-16)

·         ሕዝቦችን ከነገድ፣ ከቋንቋ ሊዋጅ
ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፣ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው (ራእይ 59)

·         ከሞት በኋላ ወዲያውኑ ከእርሱ ጋር እንድንሆን
የምንነቃም ብንሆን፥ የምናንቀላፋም ብንሆን፥ ከእርሱ ጋራ ዐብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ።(1ተሰ. 510)

·         በወንጌሉ ውስጥ የእግዚአብሔርን ኀይል ለመግለጥ
የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነውና። (1ቆሮ. 118)

·         የብሉይ ኪዳኑን ክህነት በማስቆም ዘላለማዊ ሊቀ ካህናት ሊሆን
እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኀጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጓልና። (ዕብ. 727)
ሊቀ ካህናትም በየዓመቱ የሌላውን ደም ይዞ ወደ ቅድስት እንደሚገባ፥ ራሱን ብዙ ጊዜ ሊያቀርብ አልገባም፤ እንዲህ ቢሆንስ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ ሊቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኀጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጧል። (ዕብ. 925-26)

·         ለክብሩ
በእግዚአብሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ፥ ከመላእክት ይልቅ በጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሣ የክብርና የምስጋናን ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን። (ዕብ. 29)
በታላቅም ድምፅ፦ የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ። (ራእይ 512)  

ü  ሰው በማን ዳነ?
በክርስቶስ ኢየሱስ በደሙ ቤዛነት ዳነ፡፡
ü  ሰው ለምን በክርስቶስ ዳነ?
ከፍጡር ወገንም ሆነ ከራሱ ከሰው መካከል ሰውን ሊያድን የሚቻለው ፈጽሞ መገኘት ስላልቻለ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳነን፡፡
ü  ሰው እንዴት ዳነ (ይድናል)?
“በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ” (ሐዋ.16፥31)
     እኛ ታዲያ ምን እንድርግ?
-       ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት እንገዛ ፤
-       የሐሰት ትምህርትንና በክርስቶስ ወንጌል ላይ ወንድሞች እንደቅዱስ ቃሉ እንቃወማቸዋለን ፤ ትምህርታቸውንም አንቀበል ፤
-       ልበ ሰፊ ሆነን ቅዱስ ቃሉን መመርመርና ማጥናት እናዘውትር፡፡
   እንዲህ እናምናለን ፤ እንታመናለን፡፡ “ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም” የሚለውን ትምህርት እንክዳለን፤ እንቃወማለን፤ እናወግዛለን፡፡
V  ጸጋም እንዲሁ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያመለክታል፤ ማለትም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለሰው ልጆች እንዲሁ በነጻ የተሰጠ መኾኑን አመልካች ነው፤ ምክንያቱም ጸጋ እንጂ ሕግ ሰውን የማጽደቅ ኃይል የለውምና፤ (ሮሜ.3፥21-24)፡፡

ዋቢ መጻሕፍት
·        ሃይማኖተ አበው፡፡ 1982 ዓ.ም ፤ አዲስ አበባ፤ ተስፋ ማተሚያ ቤት፡፡
·        አበራ በቀለ(ሊቀ ጉባኤ አባ)፡፡ ትምህርተ ሃይማኖት እና ክርስቲያናዊ ሕይወት፡፡ 1996 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ንግድ ማተሚያ ድርጅት (ማኅበረ ቅዱሳን)፡፡
·        ዳንኤል ክብረት(ዲ/ን) ፤ አበው ምን ይላሉ?፤ 2002 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ሜጋ ማተሚያ ድርጅት፡፡
·        ደምሰው ዘውዴ ፤ ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት አለም አይድንም  2000 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ አሳታሚው ያልተገለጠ፡፡
·        ተስፉ እንዳለ (ቀሲስ)፤ ነገረ ሥጋዌ፤ 2001 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ሜጋ ማተሚያ ድርጅት፡፡
·        የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት 6 እትም፤ 1992 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ባናዊ ማተሚያ ቤት፡፡
·        ቄስ ኮሊን ማንሰል፤ ትምህርተ ክርስቶስ፤ 3 እትም፤ 2003 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ንግድ ማተሚያ ድርጅት፡፡
·        ድርሳን ዘቅዱስ ዮሐንስ ዘአፈወርቅ፡፡ 1987 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ተስፋ ማተሚያ ቤት፡፡
·        መጽሐፈ ቅዳሴ ንባቡና ትርጓሜው፤ 1988 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ትንሳኤ ማሳተሚያ ድርጅት፡፡
·        የኢትዮጲያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት 6 እትም፤ 1992 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ ባናዊ ማተሚያ ቤት፡፡
·        John Piper, The Passion of Jesus Christ: Fifty Reasons Why He Came to Die (Wheaton: Crossway, 2004)



   [1]  John Piper, The Passion of Jesus Christ: Fifty Reasons Why He Came to Die (Wheaton: Crossway, 2004) (ጳውሎስ ፈቃዱ እንደተረጐመው)

5 comments:

  1. tebarek tru melkt new.Bitasadgewna metsaf bihon tru new.

    ReplyDelete
  2. Enter your comment...best article

    ReplyDelete
  3. well said, Honesty & beautifully written view. Thanks May the Lord Help Us!

    ReplyDelete
  4. kalehwot yasemaln tebarek abeni

    ReplyDelete
  5. በመጀመራያ የከበረ ሠለምታዬን በማስቀደም። ፁሑፍ ን ላስከትል በመጀመሪያ የፃፍከውን ሃሳብ እመንበት ከዛያ እምነትህ እንደሚያድን ስታምን አትፈራም አትደበቅም አሁን አንተ በክርስትና ሃይማኖት ተደብቀኻል ላምን ሃሳብኽ ላይ እምነት የለኽም በውስጥ ያለው ሃሳብ ትክክል ይሁን አይሁን ስላልተቀበልከው ከአንድ እውነተኝ ነው ብለኽ ከአመንከው ሃያማኖት እራስኽ ከተኽ ያላመንክበትን ሃሳብ ሰዎች እንዲቀበሉኸ ደያቆንነኝ ትላላኽ ጥነጥዬ ግዕዝ ትሞክርአለኽ የንእፅእየተ ንፁዋን የደንግል ማሪያም የእመብዙዎን የእመብርሃን የብርሃንን እናናት ስም ትጠራለኽ ሰዎቾ ሃሳብኽ አንድቀበሉኽ ያሰብከውን ሃሳብ አምነህበት ከምንም ነገር ጋር ሳታገናኝ ስትፅፍ ሰዎች በነፃነት ደስ ብሎቸው ይቀበሉኸል ብዬ ስለማምንነው ። አለበለዛያ የምትፅፈው ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፖለቲካዊ ይሆንብሃል ማለትም ሃይማኖትን መሰለል ስለሚመስል ሃይማኖትን መሰለል ደግሞ ክርስቶስን መሰለል ነው ልክ እንደ ይሁዳ ። ከዝ በፊት አንድ ዘሪሁን የሚባል ፕሮተስታንት ወደ ቀድሞ ሃይማኖቴ ተመልሻለው ብሎ በቴፕ ካሴት ላይ በሰምስክርነት ከእንግዲ በዋላ ክርስትናን ማዳከም የሚቻለው ከክርስትና ወጥቶ ሳይሆን ውስጣቸው ገብቶ በራሳቸው ቋንቋ በመናገር የተሳሳተ ትምህርት በመስተማር ነው ያለውን ነገር ያስውሰኝል ሁል ጊዜj በምርታቸው የማይተማመኑ ፋብሪካዎች ከነሱ በጥራት ከሚበልጣቸው ፋብሪካ ሰም ጋር እንደሚጣበቁት ማለት ። ለምሣሌ Adidas Adidos እንደሚደረገው ማለት ነው። የሆነው ሆ ኖ ግ ን በምድር ላይ እናት መርጦ የተወለደ ታውቃለኅ አንድ የጌቶች ሁሉ ጌታ የንጉሶች ሁሉ ንጉስ የሃያላን ሁለ ሃያል አልፍና ኦሜጋ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻና ብቻ ነው ታደያ አንተ በኢየሱስ እውነተኝ አምላክነት የምታመን ከሆነ የጌታኅን ምርጫ ወቃወም አያሆንብኅም ወይንስ ከእደቱ በእናቱ ተጀምሮ ወደ ንገሱ ይቀጥላል? ለማንኛው ቸሩ እግዚያብሔር አሰተዋይ ልብ ይስጥህ

    ReplyDelete