Saturday 7 April 2018

በ'ኛ ገኖ እንዲኖር!


ገሃነም ፈረሰ ሲዖል ተረገጠ
ኃጢአት ተሸነፈ ሞት ኃይሉ ተዋጠ
መፍረስ መበስበስም ተሻረ አበቃ
መቃብርን ሽሮ ከብሯልና ጌታ!
ከዚህ የተነሣ ...

አዲስ መንገድ ሠርቶ በደሙ መረቀ
ሾመን አከበረን ድል ነሺ አደረገን፤
ለምናምን ለኛም ሞቱን ለተካፈልን
የማያልቅ ኃይለ ሕይወት መኖርን አደለን።
እናም እንላለን ...
ለአዲሱ ዓለም ፍኖተ ካርታችን
ሕይወትን እንድ'ኖር ለሞተው ቤዛችን
ለጽድቅ ሕያው ኾነን ለኃጢአት እንቀበር
የትንሣኤው በኵር በኛ ገኖ እንዲኖር።

No comments:

Post a Comment