Wednesday 14 March 2018

እንዳትራራ ያኔ!

Please raed in PDF

ዛሬ ባንተ ጉልበት ጸጋህን ታምኜ
ከደምህ በኾነ ፍጹም ብቃት ድኜ
ስተጋ ለቃልህ ለወንጌልህ ሥራ

ባንተ አረማመዴ ሲያምር ሲያበራ
ምሕረትህን ለብሼ ምሕረትህን ሳወራ
አይቻለኹ ለኔ ለኀጥዑ ስትራራ!
አደራ ጌታዬ!
እንዲህ ተማምኜህ ነፍሴ ከሥጋዬ የተለየች ለታ
አትራራልኝ ለኔ ዝም በለኝ ላፍታ
ዛሬ ያልተማርኩትን ያኔ አትምረኝም
አሁን ያልዳንኩትን ያኔ አታድነኝም!!!

(የደብረ ዘይት ዕለት(2/7/2010) ከቅዳሴ በኋላ ቁጭ ብዬ ሳለ “አምላክ ሆይ አደራ ያን ጊዜ እንድትራራ” የሚለውን የማርታ ገ/ሥላሴን መዝሙር “ዘማሪዋ” ስትዘምር ወደኅሊናዬ እንደመጣ የጻፍኩት ግጥም)

No comments:

Post a Comment