Wednesday 8 March 2017

“የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ”

  
    ልክ ዛሬ፣ የዲያቆን አቤንኤዘር ተክሉ ገጽ በሚለው የጡመራ መድረክና(Blog) በፊት ገጽ(Facebook) መጻፍ ከጀመርኩ አራት ዓመታትን አስቆጠርኩ፤ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በጌታ ጉልበትና ቸርነት፤ በመንፈስ ቅዱስም እርዳታ ሃሳብን በማስፈር ቀስ ብዬ እየዳኽኩ፤  እያደግሁ መጥቻለሁ፤ ገና ወደፊትም ጌታ እንደረዳኝ ብዙ እንደምሠራ መሻቴ ነው፤ ግና ጌታ ብቻ እንደፈቀደ ይሁን፤ አሜን፡፡ ምኞቴና መሻቴ አንዱንና የሞተልኝን ጌታ ኢየሱስን በዘመኔ ሁሉ አክብሬ ማገልገልና ማረፍ ነው፤ ለእርሱ ኖሮ መሞት መታደል፤ እጅግ ወደር የለሽ ክብር ነው!

   በእነዚህ ዓመታት በጡመራ መድረኩ ጽሁፎች ከ600 መቶ በላይ አስተያቶች የተሰጡ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹን ለጥፌያቸዋለሁ፡፡ ከመቶ የማያንሱ የማያንጹትንና ስድብ ብቻ የሆኑትን ሌሎች እንዳያዩዋቸው[ቢያዋቸውም ስለማይታነጹባቸው] ብዬ ከመለጠፍ ተቆጥቤያለሁ፡፡
   በዚህ አገልግሎት ውስጥ[በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ውስጥ በምሰጠው አገልግሎት ውስጥ ማለቴ ነው] እንድመከርበት፣ እንድታነጽበት፣ እንድወቀስበት በብዙ ያበረታታችሁኝን ከማመስገን አልቆጠብም፡፡ በጽሁፍ ዘመኔ ከግጥም ፊቴን ወደጽሁፍም እንዳዞር የረዳኝና ያበረታታኝ፣ ውድ ወንድሜን ሙሌን መቼም አልረሳውም፤ የጻፍኳቸው ብዙ ጽሁፎች ውስጥ ያንተ “ቀስቃሽ ድምጽ” ዛሬም ይሰማኛል፤ ተባረክልኝ ከምትወደድ ባለቤትህ ሰብሊሻና ከውድ ልጅህ ጋር፡፡ ሰብሊሻ! እኒያ የሚያምሩ ሎጎዎች ያንቺ ምርጥ የምጥ ሃሳቦች ናቸውና አማኑኤል የጽድቅ ብርሃኑን በሕይወት ይሸልምሽ፤ አሜን፡፡
      መረጃዎችን በመስጠት፣ ምልከታዎችን በማሳየት፣ ቁጭትህን ሁሉ በመናገር፣ መጻፌን እንዳላቆም በማበረታታት ከጐኔ የነበርከው ውዱ ወንድሜ ሙሌ [አዲሱ ሙሽራ ሆይ!] ከልብ አከብርሃለሁ! ጌታ በነገር ሁሉ ልብህን ለመንፈሳዊ ነገር ያስፋልህ፤ ቢኒ አንተ የጡመራ መድረኩን ጽሁፎች “boost” ባታደርግ መች ለብዙዎች ደርሶ ይነበብ ነበር? ጌታ ሕሊናህንና የእጅህን ሥራ ይባርክልህ፤ ቀጫጫዋ ጄሪታ “ዛሬም ትገርመኛለህ!” የሚለው ቃጭል ድምጽሽ በአገልግሎቴ ዘወትር በብርታት እንድሮጥ ረድቶኛልና ተባረኪልኝ እላለሁ፡፡
    ጠቢቡ ሰሎሞን፣ “የማይበድል ሰው የለምና” እንዳለው ከብዙ ሰው እንደመገናኘቴና እንደመቀራረቤ በግል ጥፋቴ የበደልኳቸውና ያሳዘንኳቸው ሰዎች አሉ፤ አንዳንዶች የተቀየሙኝ በተናገርኳቸው እውነት ላይ ሲሆን፣ አንዳንዶች ግን መናገር ያለብኝን እውነት በቅንነትና በፍቅር ዝቅ ብዬ ባለመናገሬ ነው፤ ሌሎች ደግሞ ከልቤ በመሳሳት ያስቀየምኳችሁ ናችሁና በበደልኩበት መንገድ በዚሁ ይቅርታን መጠየቅን ወደድሁ፤ በእርግጥ በጊዜው ይቅርታን ለምኜያለሁ፤ ከኩርፊያችሁ ግን አሁንም ስላላገገማችሁ አሁንም ብጠይቅ ወደድሁ፡፡ ትርሲት ኃ/ጊዮርጊስ (ትርሲትና፣ ትርሲታ)፣ ሳራ፣ ሰመረ፣ ደጁ(ደ) ምናልባት የማላስታውሳችሁም ካላችሁ ይቅርታችሁን ድጋሚ ደጅ ጠናለሁ፡፡
    በተረፈ በብዙ የምትቃወሙኝና “ዓይንህን ላፈር” ያላችሁኝንም ማመስገንና መባረክ ይኖርብኛል፤ እናንተ “ባትነሳሱብኝ” መች ቆም ነበርና! ለመንቃትና ለመጠንከር ተቃውሟችሁ ትልቅ ጉልበት ሆኖኛልና፣ ጌታ በማስተዋል እንዲባርካችሁ ትልቅ ትጋቴ ነው፤ የያዕቆብ አምላክ ተወዳጁ የእስራኤል ቅዱስ ፊቱን ያብራችሁ፤ ይራራላችሁ ፤ አሜን፡፡
      “ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመጥፋት ከሚወዱ ሁሉ ጋር ጸጋ ይሁን፤ አሜን፤ (ኤፌ.6፥24)፡፡ 

8 comments:

  1. ቃለ ሕይወት ያሰማልን ወንድማችን

    ReplyDelete
  2. ጌታ ኢየሱስ ዘመንህን ይባርክልህ አገልግለኸው እንድታርፍ እርሱ ይርዳህ፡፡ በበረከት ተትረፍረፍ

    ReplyDelete
  3. Wendeme Dengele keneljwa abzeta tebrkeh!!! MESEKREM NEGN k Dallas,Tx

    ReplyDelete
  4. Yetewededk Wendeme Dengle kenelgwa tebarkeh!!! Leberket hune.

    ReplyDelete
  5. This comment has been removed by the author.

    ReplyDelete
  6. ወንድሜ የእግዚያብሔር ፀጋ በዘመንህ ሁሉ ይሁን።

    ReplyDelete
  7. tebarek wendm rejm edme yistih agelgilotih ybarek

    ReplyDelete
  8. ጌታ ይባርክህ ይቀድስህም
    ለህይወትህ ልምላሜን ይስጥ
    ጸጋውን በእጥፍ እጥፍ ያብዛልህ
    ቅንነትህን ይባርክ። በዘመንህ ሁሉ ሃሌ ሉያ የምስጋና ድምጽህ ማሰሪያ ይሁን

    ReplyDelete