Monday 13 March 2017

አትተወን

የትዳር አልጋችን ረከሰ ከየሰ
የኪዳን ቃላችን ሳይውል ፈራረሰ
ከባልንጀራ ጋር በሐሜት ተራኩተን
አንድ ነን እያልን አለቅን ተበላልተን፡፡

አቤቱ!
ክርስትናው ምግባር እምነቱ አማኝ አጣ
“መጻጉአን በዛን” ነፍሳችን ሞገገች፣
                         ሥጋችን ገረጣ
አቤቱ አሁን አድን አቤቱ አሁን አቅና
መጻጉን የፈወስክ ኢየሱስ ቶሎ ና!

ማራናታ!

3 comments:

  1. አሜን! አሜን! አሜን! ተባረክ በብዙ ይባርክህ

    ReplyDelete
  2. ቃለ ሕይወት ያሰማህ ወዳጄ

    ReplyDelete
  3. Geta lezelalem bebetu yabrtahe wendeme

    ReplyDelete