Tuesday 10 November 2015

ከፍቶታል በሩን






የሴቲቱ ዘር፥ የእባቡን ራስ ʼሚቀጠቅጠቀው፤
የአብርሃም ዘር፥ የምድርን ነገድ የሚባርከው፤
ከዳዊት ወገብ፥ በትር የሚሆነው ለምለም ቁጥቋጦ፤
የተወለደው፥ እኛን ሊወልደን ከሕዝብ መርጦ፤
የጽድቅን ፍሬ፥ ለአለሙ ሁሉ በደም ሊያፈራ፤
ተወለደልን፥ በቤተ ልሔም፥ በእንሰሳቱ  የበረት ሥፍራ፡፡
የምሥራች ነው፥ ድምጹን በግርግም ያሰማን ህጻን ፤
ማንም ላይዘጋው፥ ከፍቶታል በሩን የአዲሱን ኪዳን፤
መግባት መውጣት ነው፥ በʼርሱ በርነት ፤
ወደእርሱ የገባ፥ አያገኘውም ውርደትና ሞት፡፡

1 comment:

  1. አሜን አሜን ....... በርሱ በርነት ወደርሱ የገባ አያገኘዉም ውርደትና ሞት! ተባረክ ዎዳጂ!

    ReplyDelete