Thursday, 22 January 2015

ዕድሜና ፍሬያችን


                                      Please read in PDF

ከትላንት በስቲያ …
አሜሪካ ʻምትባል ትልቅዬ አገር
በአንድ መልሳ ፣ የሥጋ መንፈስዋን ፣ ክፍልፍሉን መንደር
ʻስቴቶቿን ሁሉ ቀምራ አዋህዳ
ተተኮሰች “አሉ” አድጋ ተመንድጋ
እኛን እዚህ ትታ እርሷ ወደህዋ …
 አሁን በቀደም ʻለት ትንሽዬ አውራጃ
ዱባይ የምትባል ቀዬ ተመስርታ
ሕልም እስክትመስል በጥበብ ጐልምሳ
ታየናለች ይኸው ከላይ አጎንብሳ፡፡

እኛ ግን …
ሦስት ሺህ ዘመናት ትግትልትሉን ዕድሜ
የት ነው ያሳለፍነው የት ነበርን አዳሜ?
ዘር ቆጠራ ላይ ነን ወይስ ጦርነት ውስጥ?
እግዚእ ጌታን ትተን ብሔር ስናማርጥ
ጥሎን ሄደ አለም ፣ ስʻኖር በፉክክር ፣ በማለት እኔ እበልጥ፡፡
የት ነበርን ከማን ጋር ምን ስንሠራ ሸበትን
ድሪቶ ሳንቀይር እንዴት ጎብጠን ታየን?
ወዴት ራቀን ድንገት ትልቅነታችን?

ከእግዜር ጋር አድገናል ኖረናል እያልን
የታʻል ምስክሩ የመኖር መልካችን
አይመሳሰልም ዕድሜና ፍሬያችን?
ዛሬም …
አልመሸም ሊመጣ የጥንቱ መልካችን
ግና …
ንስሐን ከቀደምን ያው ነው ጥረታችን!


1 comment:

  1. Thanks for any other informative blog. Where else may I get that type of information written in such a
    perfect means? I've a undertaking that I am simply now running on, and I have been at the glance out for such
    information.

    my web blog; kitchen renovation ideas [homeimprovementdaily.com]

    ReplyDelete