ይህ ጽሁፍ በዚህ
ብሎግ በመጀመርያ ሲወጣ ተቃዋሚዎች ገጥመውታል፤ በተቃውሞው ምክንያትም ለጊዜው ከዚህ ብሎግ ላይ ለማንሳትና ያለውን ነገር ለማጤን
ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ነገር ግን ቁጣውና ተቃውሞው ለእግዚአብሔር ስላላደላና ኃጢአትን ስላልተቃወመ ምንም ሳልቀንሰው ሙሉ ጽሁፉን
እንዳለ መልሼ አውጥቼዋለሁ፡፡ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው ፊት አናደላም፤ የሚያስጨንቀን የቤተ ክርስቲያን ቅድስናና ሸክም እንጂ
በእግዚአብሔር ምህረት ላይ ለሚዘብቱና ለክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን መነቀፍ ግድ ለማይላቸው አይደለም!!!
ስለግብረ ሰዶም ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር ጉልበት ቤተ ክርስቲያንን ስለሚያሳድፍ
ስለየትኛውም ነውር ለክርስቶስ አድልተን ከመገሰጽ ዝም አንልም፡፡ ግብረ ሰዶም አገር እያካለለ ለመሆኑ የቅርብ ሌላ ማሳያ ብናመጣ፤
ሬድዮ ፋና “የአመቱ የፍቅር አሸናፊ ግጥም” ብሎ በግዮን ሆቴል በሸለመው ሽልማትና በራሱ ሬድዮ በትላንትናው ዕለት የለፈፈው ከሴት
ለሴት የተጻፈ “የፍቅር ግጥምን” ነው፡፡ መቼም በአገራችን የፍቅር ግጥም ብሎ ከሴት ለሴት የሚጻፍ ይኖራል ብሎ ማሰብ ወይ የአገርን
ባህል መናቅ፤ ወይ ግብረ ሰዶምን መደገፍ እንጂ ሌላ ትርጉም አይሰጠውም፡፡
ይህንና ሌላም እየሰማን ዝም ለማለት የተቀበልነው አደራ አይፈቅድልንም፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ስለግብረ ሰዶማዊነት
በሁለት የተለያዩ ክፍሎች መጻፌና በሁለቱ ክፍሎችም ለጊዜው የነበረኝን ሃሳብ ማጠቃለሌን አልዘነጋውም፡፡ ነገር ግን አሁንም
ግብረ ሰዶማዊነት የቤተ ክርስቲያንን ቅድስና ከማርከስ፤ ምድራችንን ለከፋ ጉስቁልናና ርኩሰት አሳልፎ ከመስጠት ያላቆመ ፍጹም
ወደመስፋፋት የሄደ ክፉ ርኩሰት ነውና ዳግም ይህንን ርዕስ ማንሳት አስፈልጎኛል፡፡ ለዚህ እውነታ ብዙ የቅርብ ጊዜ ማሳያ ብቻ
ማንሳቱ በቂ ይመስለኛል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቁ የሃገራችን ክፍል ነው፡፡ የሠላሳ ሁለት አመት አጐት የአራት አመት የወንድም ልጁን
በእረኝነት ሥፍራ በመሄድ ጫት እንዲቅም ያግባባዋል፡፡ ህጻኑ እንቢ ቢልም ያስገድደዋል፡፡ ጫት እንዲቅም ካስገደደው በኋላ ልጁ
ራሱን መቆጣጠር ሲያቅተው ልጁን የግብረ ሰዶም ጥቃት ይፈጽምበታል፡፡ የልጁ የሰገራ ማውጫ ሙሉ ለሙሉ ይቀዳዳል፡፡ ከሆዱ የወጣው
የውስጠኛው የሰገራው ክፍል ሙሉ ለሙሉ የልጁን ጠረን ይለውጠዋል፡፡ ልጁ ፍጹም ራሱን ስቶ ሲወድቅ ከወደቀበት ቦታ ተሸክሞት
ከወላጆቹ ጓሮ አምጥቶ ጥሎት ይሰወራል፡፡ ከዚያ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የልጁ ህይወት ያልፋል፡፡
ሌላም ብንጨምር፦ አንድ “ስመ ገናና” አገልጋይ እንዲህ ያለ ነውር እንደሚፈጽም በምስክር ይረጋገጥና ብዙዎች ተረባርበው ሊመክሩት ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ከማስመሰልና የሽንገላ እሺታ ከማሳየት በቀር ከነገሩ ሳይታቀብ ይቀራል፡፡ በኋላ ይባስ ብሎ በአቋም፤ የሠራው ትክክል እንደሆነና ይቅርታ መጠየቅ እንደማያስፈልግ ከብዙ ደጋፊዎቹ ጋር በግልጥ በአቋሙ ይጸናል፡፡ ወንድሞቹን ይቅርታ ሳይጠይቅ በግልጥ ለሠራውና ሌሎችን ላሰናከለበት ኃጢአቱ ንስሐ ሳይገባ እንደዋዛ ዛሬም አለ፡፡ በድርጊቱ የተጠቁት ወንድሞች ግን “እንዲህ ያለ ነገር እያደረገ በአንድ የኃይማኖት ጥላ ሥር አንቀመጥም” በማለት ወደሌላ የእምነት ተቋም ራሳቸውን አገለሉ፡፡ (ርቀው ወደሌላ የኃይማኖት ተቋም እንዳይሄዱ ብዙ ርብርብ ቢደረግም አልተሳካም፡፡)
በመንግስትም ደረጃ በዘንድሮው የይቅርታ መመሪያ ውስጥ ይቅርታ ከሚያሰጡ ወንጀሎች መካከል ግብረ ሰዶማዊነትም እንዲካተት ጥረቶች
“መደረጋቸውና መሳካቱንም” ጭምጭምታዎች ይሰማሉ፡፡ ጉዟችን ወዴት ይሆን? እንዲህስ እስከምን ድረስ ነው የምንጓዘው?
ግብረ ሰዶማዊነት እግዚአብሔር የፈጠረውን ፍጥረት ሙሉ ለሙሉ በመቃረን የሚፈጸም ርኩሰት ነው፡፡ ቃሉም “ስለዚህ እርስ
በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው”(ሮሜ.1፥24) እንዲል ቅዱሱን
የእግዚአብሔር ፍጥረት በመቃረናችን ምክንያት የገዛ ኃጢአታችን “ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ እንደሰጠን” ትልቅ ምስክር
ነው፡፡(ሮሜ.1፥26)
ጥቂት
የማይባሉ አገልጋዮች “ለአገልግሎት” ወደክፍለ አገር ወይም ወደውጪ አገር ሲወጡና ጨርሰው ሲመለሱ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ሹልክ
ብለው ለሴሰኝነትና ለዝሙት እንደሚገባበዙ ፀሐይ የሞቀው እውነት ሆኗል፡፡ በአቶ አስማማው ኃይሉ በተጻፈውና
“ኢህአሠ” በተባለው ቅጽ አንድ መጽሐፍ ላይ ከትግል መልስ ደራሲው አንድ ታጋይ ነገረኝ ብሎ ሲጽፍ ፤ ታጋዩ ማደሪያ አገኘሁ
ብሎ ወደ አንድ ቤተ ክርስቲያን ሊጠለል ጎራ ባለበት ወቅት ሌሊቱን ሙሉ የገጠመው ሌላ ትግል ይኸው ከግብረ ሰዶማውያን
ጋር ያደረገው ያለመደፈር ትግል እንደነበር በግልጥ አስቀምጦታል፡፡ በእርግጥ ዛሬ በገዳም ካሉት ጥቂት የማይባሉ መነኰሳትና
መነኰሳይያት፤ እንዲሁም በወንዶችም ሆነ በሴቶችም ዘማሪዎቻችን መንደርም የምንሰማው ነገር ጆሮን ጭው የሚያደርግ
ነው፡፡ (እንደአገር ስናስብ ደግሞ በካርዲናሎቹና በፓስተሮቹም መካከል አጸያፊ የርኩሰት ነገር ጆሯችን ከመስማት አልታከተም!!)
ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ ኃጢአተኞችን በግልጥ ከመቃወም እየደከመች የመጣች ይመስላል፡፡ ምክንያቱም የግብረ ሰዶማውያን
“አገልጋዮችን” የጨለማ ሥራን ከመግለጥ (ኤፌ.5፥11)፤ ሌሎች ሰዎችም ከክፋታቸው እንዳይተባበሩ ከማስጠንቀቅና መክራ
እንዲመለሱ ከማድረግ ድምጿን አሰልላለች፡፡ ስለዚህም ሌሎች ብዙዎች ግብረ ሰዶማውያኑን “በርቱ፤ እኛም ከጎናችሁ ነን”
ከማለት አልፈው ለግብረ ሰዶማውያኑ ድጋፍ ሲሰጡና ሲሟገቱላቸው በአይናችን እያየን ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ኩልልና ጥርት ያለ
የተቃውሞ ድምጿን ልታሰማ ግድ የሚላት ጊዜ አሁንና አሁን ነው፡፡ ከረፈደ በኋላ መሯሯጥ ድካም እንጂ ሚዛን የሚደፋ ትውልድ
የማዳን ሥራ አይሠራም፡፡
የሰዶም ሰዎች ያደርጉት የነበረው የክፋት ድርጊታቸውን እንደመልካም ከመቁጠር አልፈው እነርሱ የሚያደርጉትን ነውር
የማያደርጉትን ሰዎች ይቃወሙ፤ የእነርሱን ነውር እንዲቀበሉ ያደርጉም ነበር፡፡ በአገሪቱ ካሉት ሰዎች ሁሉ ጋር ነውራቸውን
ከፈጸሙ በኋላ እንግዳ ሰዎች በመካከላቸው በተገኙ ጊዜ ከእንግዶቹ ጋር ሊፈጽሙ (በሎጥ ቤት የመጡትን መላዕክት ሲያዩ
ወደአዲስ መጎምጀት መጥተዋልና!) የኃይልን መንገድ እንደተጠቀሙ፤ ጻድቁንም ሎጥ እንደተጋፉትና በሩን ሊሰብሩ እንደተገዳደሩ
ታላቁ መጽሐፍ ይነግረናል፡፡(ዘፍ.19፥5-9) ሰው ለእግዚአብሔር ባህርይና ለተፈጥሮ እውነት መገዛት ሲሳነው የኃጢአት መሻቱ
ድንበር አልባ ይሆናል፡፡ ሁሉንም ርኩሰት ከመፈጸም የሚያግደውም የለም፡፡
ዛሬ ላይ
ድሆች ሃገራትን ለመርዳት የሚዘረጉ ብዙ የእርዳታ እጆች ስውር አጀንዳቸው ግብረ ሰዶምና ሰዶማዊነት ለመሆኑ ብዙ ማስተንተኛ
ማቅረብ አያስፈልግም፡፡ ግብረ ሰዶምን በግልጥ የተቃወመች ብቸኛይቱ አፍሪካዊት ሃገር ይህንን በግልጥ አይታዋለችና፡፡ እኛ
“ከቃል ባልዘለለ” ክርስትናችን በከንቱ ስንመካ ከአገራችን ቀድማ ግብረ ሰዶማዊነትን በግልጥ አለም አቀፍ በሆነ ዕይታ ህግን
አስደግፋ ተቃውሞ ያሰማችው አፍሪካዊት አገር ኡጋንዳ ናት፡፡ በእርግጥ የእኛ ወንጀል ህግ “ግብረ ሰዶማዊነት ወንጀል ነው”
ይላል፤ ግን የአገሪቱን ትልልቅ ከተሞች ጎዳና እያጥለቀለቁ ያሉትና ቁጥራቸው የማይናቅ አገልጋዮችን እንደወረርሽኝ በሽታ
እየወረሱት ያሉት “ሴት እንተኛ አዳሪዎች” ብቻ ሳይሆኑ ግብረ ሰዶማውያኑም ጭምር ናቸው፡፡ ህጉ ቢኖርም ለነዚህ ምድርን
ለሚያረክሱ “ወገኖች” ግን ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖ ተቀምጧል፡፡
የኡጋንዳ
መሪዎች ያንን የመሰለ ቁርጥ ያለ አቋማቸውን በግብረ ሰዶማዊነት ላይ ሲያሰሙ፤ ሰለጠን ያሉቱ ምዕራባውያን የኡጋንዳን ድርጊት
“የሰይጣን ድርጊት” አድርገው ለማቅረብ ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ (እግዚአብሔርስ ይቅር ሰይጣን እንኳ እንዴት ታዝቦን ይሆን?!)
የእኛ አገልጋዮች ግን ዛሬም ግብረ ሰዶማዊነትን በመካከላችን ያሽሞነሙኑታል፡፡ ከዓመታት በፊት ግብረ ሰዶማውያኑም
አለም አቀፍ ስብሰባ አፍንጫችን ስር ባለችው አዲስ አበባ አድርገው አባላታቸውን መልምለው ሲሄዱ እንኳ ዝም ጭጭ ሆኗል
ክርስትናችን፡፡ እንኪያስ ወርቁ ለምን ይሆን የደበሰው?
ግብረ
ሰዶማውያንን ለመቃወም የአገልጋዮች “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ” ማለት ከበለጠብን እንኪያ እኛስ ከእነርሱ በምን እንሻላለን?
መንፈሳዊነት መለኪያው የአገልግሎት ስኬት ሳይሆን የህይወት ጥራት ነው፡፡ ጌታ ጥራት ከሌለው ሸንጋይ መንጋ ጋር ህብረት
እንደሌለውና ጥራት ካለው ጥቂት አማኝ ጋር ብቻ ህብረት እንዳለው በጌዴዎንና በሐዋርያት ህይወት አይተናል፡፡ ምክራችን፣
ጩኸታችን፣ ተግሳጻችን፣ ቁጣችን … “ምክር ለምኔ” ያሉ ግብረ ሰዶማውያን አገልጋዮች በንስሐ ተመልሰው የበደሏቸውንና
ያሰናከሏቸውን ወንድሞች ይቅርታ በመጠየቅ እንዲመለሱ ነው እንጂ በመካከላችን ተቀምጠው ሌሎችን ለማጥቃት እንዲያደቡ አይደለም፡፡
የእግዚአብሔርን ምህረት የሚያሸንፍ ወይም የሚበልጥ ኃጢአት የለም፡፡ እንዲህ የምንለው ግን በንስሐ ለሚመለሱ እንጂ
ልብን ለሚያደነድኑ አመጸኞች አይደለም፡፡ ጌታ ለምድሪቱ ምህረትና የንስሐን ልብ ያውርድላት፡፡ አሜን፡፡
wonderful. sin is sin. don't fear some people who r worshiping a ``preacher`` u always should stand with the word of God. i appreciate you. be blessed,
ReplyDeleteወንድሜ ኀጢአትን ሀጢአት ለማለት ላበረታህ መንፈስ ቅዱስ ክብርና ምስጋናን እሰጣለሁ። ግብረሰዶማዊነት ደግሞ ደፍረው ካልተቃወሙት አደጋው ከባድ ነው። በሰዶማዊያን ዙሪያ ያሉ ሰዎች ለጥቂት ጊዜም ቢሆን ጽሁፉን እንድታነሳው ከተቃወሙህ ሀጢአቱ ምን ያህል ደፋር ሰዎችን እየወለደ እንደመጣ ያሳየናል። እውነት ዋጋ ማስከፈልዋን ሳትረሳ ሀጢአትን በድፍረት መቃወሙን ቀጥልበት።
ReplyDeletewey girume sedomawinet endihe egeza yideregeletal malet new? yasazenal. ante gin wendem ayzohe leewnet kum
ReplyDeleteAnte tekula semhen keyerew pastor tehonaleh engi diakon adelehem
ReplyDeleteምን ማለት ነው? ዘለህ ስድብ ከመለጠፍ የተጻፈው መልዕክት ምን ይላል ብለሀ ብትናብና ብትረዳ አይሻልም? ነው ነገሩ ይመለከትሃል?
Deleteተባረክ ወንድም ጥሩ ጽሁፍ ነው
ReplyDeletelemindenew wede nesiha yewmayimelesut eyaderegu yalut tikikl new bilo yemiyamnut ?
ReplyDeleteእንቅልፋም ሁሉ ጓዳ ጓዳውን ሲሽከረከር በድፍረት ይህን ነገር ለመቃወም በመቻልህ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ። ከጠላት ውጊያና ፈተናም ይጠብቅህ
ReplyDeleteወንድሜ ጌታ ይባርክህ። ይሕን በመጻፍህ ብዙ ተቃውሞ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ሊገጥምህ ይችላል ቢሆንም የእግዚአብሔር ሀሳብ ስለሆነ ክፉውን ከመቃመም ቸል አትበል። ጌታይጠብቅህ
ReplyDeleteEgziabhier yibarkih wondim yich alem malfiyawa dersual gin be dingel maryam ager be melkt ager endih aynet sira betam yasazinal
ReplyDeleteEGZIABHER YIBARKIH CHIGIRU EKO EYEBASE YEMETAW ENDEZIH BEGILT YE GUDAYUN ASASABINET LEMENAGER,LEMEKAWEM YALEMEDFERACHIN NEW BEMENGISTIM BE HYMANOTIM BE GILESEBIM DEREJA E/R MELKAMUN HULU YAMTALIN
ReplyDeleteAmen Ewnet new
Deletegood job
ReplyDeletegebersadomen mkawmeh teru naw endande saw gene ahunem kbitkeresetiyanachen laye warde bale uayemanotachenene lamnekfe yamatargwe yalme gen eko tekekelga tamlekache khoneke malte naw bdubaye wesete ymiyaglgelute yanet ythdeso abaloche eko nacwe yehine eyargu yalute lamen atawgezacwem ? thdeso eyalcu yamatamtute nagre yalme bitkeresetiyanachenn lmbtane yamatrgute nagre yalme ahune damo gebtsdomen wdabitkeresetiyanachene letamtubene btame yaszenal;
ReplyDeletebtame yegremal
ReplyDeletebetam adnakihna degafih negn! ketlbet berta! gibre-sodomawinet ye-AYHUD tegbar new!enam hatiyatn bemeqawemih berta litbal yigebal.wede Ethiopia hagerachin yemimetu AYHUDOCHIN bemeqawem gibre-sodomawinetn mekelakel yichalal::
ReplyDeleteሃጢያትን በመቃወምህ ቁጥር አንድ አድናቂህ ነኝ! በርታ! ፈጣሪን እንጅ ማነንም አትፍራ:: ግብረ_ሶዶማዊነት የአይሁድ ተግባር ነው፡በመሆኑም ወደ ሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች በልማት ሰበብ የሚገቡ አይሁዶችን በመከላከል ግብረ_ሶዶማዊነትን ከመስፋፋት መከላከልና ትውልድን ከቁም ሞት ማዳን ይቻላል::
እግዚይብሄር ይባርክህ!
Egzabehear bekutawe sedomena gomoran enedatefachew enezihenem yeatefachewale. Ye Egzabehear keale ewenet newena. Egzabehear yemesegen selehuluem neger
ReplyDeleteበርታ ወንድሜ አሁንም ሰማይ ይከፈትልህ።
ReplyDelete